በኢትዮጵያ ፈጣን የከተሞች መስፋፋትን ተከትሎ የከተማ ነዋሪዎችንና የሌሎች ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማጠናከር መልካም ተሞክሮዎችንና ልምዶችን በማስፋፋት የከተማ ልማት ፖሊሲውን እና የከተማ ልማት ፕሮግራሞችን ትግበራና ስኬት ማፋጠን ይቻል ዘንድ ቀደም ሲል ዓመታዊ የከተሞች ቀንና ሳምንት በመባል ተሰይሞ በተለያዩ ከተሞች አስተናጋጅነት በየዓመቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲከበር የቆየ ሲሆን በ2009 በጀት ዓመት የከተሞች ፎረም በሚል በዓሉን በጎንደር ከተማ ይከበራል፡፡
የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረምን በገንዘብም ሆነ በአይነት ድጋፍ እንዲያገኝ በማድረግ ከተሞች የልማት ስራዎቻቸውን የሚያሳዩበትና ገጽታቸዉን የሚገነቡበት፣ እርስ በእርስ የሚማማሩበት፣ ለኗሪዎቻቸው እና ለሌሎች ባለ ድርሻ አካላት አስፈላጊ መረጃ የሚሰጡበት እንዲሁም የኢንቨስትመንት፣ የኢንዱስትሪ፣ የቱሪዝም፣ የገበያ እና ሌሎች መስህቦቻቸውን የሚያስተዋውቁበት መድረክ በመፍጠር ለዕድገታቸው መፋጠን አጋዥ የሚሆኑ ግብዓቶችን እንዲያገኙ ማስቻል አስፈላጊ በመሆኑ የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ስፖሰር አድራጊዎችን ሚና በመለየት በጎንደር ከተማ ለ7ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም የገቢ ማሰባሰብ ሥራው የሚመራበትን ስርዓት ለመደንገግ ታሳቢ በማድግ ተዘጋጅቷል፡፡