የመመሪያ መለያ: 732/2013
ቀን: የካቲት 12፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

6ኛው የኢተዮጵያ ከተሞች ፎረም የፋይናንስና ሎጂስቲክ አቅርቦት አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 732/2013

በኢትዮጵያ ፈጣን የከተሞች መስፋፋትን ተከትሎ የከተማ ነዋሪዎችንና የሌሎች ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማጠናከር መልካም ተሞክሮዎችንና ልምዶችን በማስፋፋት የከተማ ልማት ፖሊሲውን፣ ፕሮግራሞችንና ፕሮጀክቶችን ትግበራና ስኬት ማፋጠን ይቻል ዘንድ አመታዊ የከተሞች ሳምንት የተሰየመ ሲሆን፣ በዚሁ መነሻነት ላለፉት አምስት አመታት በየዓመቱ በተለያዩ ከተሞች የተካሄደ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ 6ኛዉ የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም በሚል በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር በህዳር ወር 2007 ዓ.ም ይከበራል፡፡

ማንኛውም ተቋም የተሰጠውን ተግባርና የተጣለበትን ኃላፊነት በሚገባ ሊያከናውን የሚችለው የተጠናከረ የገቢ ምንጭና በትክክል የተደራጀ የፋይናንስና አቅርቦት አመራር ስልት ሲኖረው መሆኑ አጠያያቂ አይደለም:: የተደራጀና የተጠናከረ የፋይናንስና አቅርቦት አመራር ሲባል አንድ ተቋም የሚሰበስበውን ገቢ፣ የሚያወጣውን ወጪና አቅርቦት እንዴት በተግባር ላይ እንደሚያውለው የሚከተለው የአሠራር ስልት ማለት ነው:: ለዚህም የፋይናንስ ዕቅድና የፋይናንስ አያያዝ መመሪያዎችን እንዲሁም የአቅርቦት አፈጻፀም መመሪያ ማዘጋጀትና ሥራ ላይ ስለሚውልበት ሁኔታ አመቺ ስልት መቀየስ፤ የተሟላና ተገቢ ይሆነ የሒሳብና የአቅርቦት መዝገብ አያያዝና ሪፖርት አቀራረብ ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡

ስለሆነም 6ኛውን የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም ዝግጅት በአግባቡ ለማካሄድ የሚሰበሰበውን ገንዘብ በኃላፊነት እንዲመራ የተደራጀ ኮሚቴና የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ሥራቸውን ሲያከናውኑ የሚፈለግባቸውን ተግባር ጠንቅቀው ሊያውቁ ይገባል፡፡ ከዚህ አኳያ የሚያከናውኑትን የዕለት ተዕለት ሥራ በአግባቡ ለማከናወን የሚረዳ የፋይናንስና ሎጂስቲክ የአቅርቦት አፈፃፀም መመሪያ ሊኖር ይገባል፡፡ በዚህም መሠረት ይህ አጭር የፋይናንስና ሎጂስቲክ የአቅርቦት አሠራር መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን

Ministry of Urban and Infrastructure

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration