በኢትዮጵያ ፈጣን የከተሞች መስፋፋትን ተከትሎ የከተማ ነዋሪዎችንና የሌሎች ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማጠናከር መልካም ተሞክሮዎችንና ልምዶችን በማስፋፋት የከተማ ልማት ፖሊሲውን እና የከተማ ልማት ኘሮግራሞችን ትግበራና ስኬት ማፋጠን ይቻል ዘንድ አመታዊ የከተሞች ሣምንት የተሰየመ ሲሆን የኢትዮጵያ ከተሞች ሣምንት በተለያዩ ከተሞች አስተናጋጅነት በየዓመቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚከበር ይታወቃል፡፡
ከኢትዮጵያ ከተሞች ሣምንት አበይት ክንውኖች መካከል ከተሞችን መንግሥት በነደፋቸው ስትራቴጂዎች አፈፃፀምና ያከናወኗቸው ተግባራት ከበኣሉ ተሳታፊዎች ጋር ራስን የማስተዋወቅ ሥራ አንዱ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ከተሞች በአለፉት ዓመታት በተፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ ከፍተኛ እድገት ያስመዘገቡበትና ለሀገራዊ ምጣኔ ሀብት የሚሰጡት ግብዓት ከፍ ያለበት ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን ይህም ከተሞች ለኢንቨስትመንት፣ ለገበያ፣ ለቱሪዝም ወዘተ በራቸውን እርስ በእርስ ብቻ ሳይሆን ከዓለም ከተሞችም ጋር ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት ይጠበቅባቸዋል። ይህ ውድድር ከተሞች እድገታቸውን ለማፋጠንና የኗሪዎቻቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ ከ726/2013 – በተጨማሪ ብቃት ያለው ራስን የማስተዋወቅ (Professional City Marketing) ስራን የሚጠይቅ ነው፡፡ ስለዚህም ከተሞች ከመቼውም ይበልጥ የተደራጀና ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃን በጠበቀ መልኩ ራሳቸውን የማስተዋወቅ እና የመሸጥ ሥራን አጠናክረው ማከናወን ይጠበቅባቸዋል። የኢትዮጵያ ከተሞች ሣምንት ይህንን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የከተሞቻችንን ራስን የማስተዋወቅ ሥራ ለማገዝ ይቻል ዘንድ ሀገር አቀፍ የኢትዮጵያ ከተሞች ኤግዚቢሽን በኘሮግራሞቹ አካቷል።
በመሆኑም ይህንን የከተሞች ራስን ማስተዋወቅ ሥራ ይበልጥ ለማጎልበት በውድድር መልክ እየተዘጋጀ የላቀ ደረጃ እንዲደርስ መደረግ አለበት፡፡ ከዚህ አኳያም ከተሞች በዘርፉ በተለዩ ሰባቱ ዓምዶች (በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በመሬት ልማት ማኔጅመንት፤ በከተሞች መልካም አስተዳደርና አቅም ግንባታ፣ የመኖሪያ ቤቶች ልማት፣ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ፤ የከተሞች መሠረተ ልማት አቅርቦትና ስራ አመራር፣ በከተሞች ፕላን፣ ፅዳትና ውበት አፈፃፀም አንፃር ያላቸውን ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ሲስተዋውቁ ውድድሩን በአግባቡ ለመምራት የሚያስችል መስፈርት ለማዘጋጀት ይቻል ዘንድ ይህ መመሪያ ተዘጋጅቷል።