ዳይሬክቶሬቱ የፍትሕ ሚኒስቴር ሰራተኞችን ስነ-ምግባር በመገንባት ፣ የብልሹ አሠራር ተጋላጭነትን መቀነስ የሚያስችሉ የሰራር ስርዓቶች እንዲቀረጹ ክትትልና ድጋፍ በማድረግና የስነ-ምግባር መዛነፍን ለመከላከል ተጠያቂነትን ማረጋገጥ የሚቻልባቸውን ስርዓቶች በመዘርጋት የፍትሕ አገልግሎቱ ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል የተቋቋመ የስራ ክፍል ሲሆን፡-
በአዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 11 እና አንቀጽ 19፣ በአዋጅ ቁጥር1236/2013 እንዲሁም በደንብ ቁጥር 144/2000 እና መመሪያ ቁጥር 20/2013 መሠረት የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል።
- የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች በስነ-ምግባርና ሙስና መከላከል ያላቸውን ክፍተት በጥናት ይለያል የሥልጠና ሰነድ ያዘጋጃል ፣ ተግባር ተኮር ሥልጠና ይሰጣል።
- በመልካም ስነ-ምግባር ግንባታ ፣ በሙስና መከላከል ስትራቴጂዎች በተለያዩ የስነ-ምግባርና የጸረ -ሙስና ጉዳዮች ላይ ለሰራተኞችና አመራሮች ሥልጠና ይሰጣል።
- የተቋማት ስነ-ምግባር መመሪያ ያዘጋጃል ፣ እንዲጸድቅ ያደርጋል ፣ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል።
- በመልካም ስነ-ምግባርና ሙስና መከላከል ዙሪያ ግንዛቤ የሚፈጥሩ የተለያዩ የሚዲያ መልዕክቶች እንዲዘጋጅ ያድርጋል ፣ ያሳትማል ያስተላልፋል።
- በስነ-ምግባራቸው የተመሰገኑና ለሌሎች አርአያ የሆኑ ሰራተኞችንና አመራሮችን በመመሪየው መሠረት በመለየት የእውቅና መድረክ ያመቻቻል ፣ እውቅናና ማበረታቻ ሽልማት እንዲያገኙ ያደርጋል።
- በተቋሙ ውስጥ የሚሾሙ ወይም የሚመደቡ ወይም የሚቀጠሩ የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ስራ ከመጀመራቸው በፊት የስነ-ምግባርና ሙስና መከላከል ሥልጠና ይሰጣል።
- በስነ-ምግባር ግንባታና በሙስና መከላከል ድርሻ ካላቸው አካላት ጋር የስራ ግንኙነት እንዲፈጠር ያስተባብራል።
- ለሙስናና ብልሹ አሠራር የተጋለጡና ሊጋለጡ የሚችሉ የአሠራር ስርአቶችን ማጥናት ወይም እንዲጠኑ ማድረግ ፣ የተሰጡ የመፍትሔ ሀሳቦችን ማቅረብ ፣ ተግባራዊ መሆናቸውን መከታተል ፣ በማይፈፅሙት ላይ ተገቢ የሆነ እርምጃ እንዲወሰድ ለኮሚሽኑ ማሳወቅ፣
- በተቋሙ ውስጥ የሚገኙ የሕዝብ ተመራጮች ፣ የመንግሥት ተሿሚዎች የመንግሥት ሰራተኞች ፣ መንግሥት የልማት ድርጅቶች የስራ ሀላፊዎች እና ሰራተኞች ከተሰጣቸው ሃላፍነት ፣ ከመቆጣጠርና ከመወሰን ሥልጣን ጋር በተያያዘ የሚፈጠር የጥቅም ግጭትን በጥናት ይለያል ፣ የመከላከያ ዘዴዎችን ያመነጫል ፣ ተግባራዊ ያደርጋል።
- በተቋሙ ውስጥ ሙስና ለመፈጸም የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ሲገመት ወይም ሲጠረጠርና ጥቆማ ሲደርሰው ደርጊቱ ከመፈጸሙ በፊት ኮሚሽኑንና የተቋሙን የበላይ ሀላፊ በማሳወቅ አስቸኳይ ሙስና መከላከል ስራ ይሰራል ፣ ሂደቱ እንዲቋረጥ ወይም አስፈላጊውን ማስተካከያ እንዲደረግ ያደርጋል። ሆኖም ግን በተደረገው የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ተግባር ሙስና ስለመፈጸሙ ጥርጣሬ ሲኖረው በሕግ የመመርመርና የመክሰስ ሥልጣን ላለው አካል ያሳውቃል፤
- በተቋሙ አዲስ የተሾሙ ፣ የተቀጠሩ አመራሮችና ሰራተኞች ስራ ከመጀመራቸው ወይም የቅጥር ፎርም ከመሙላታቸው በፊት ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ያድርጋል፤
- በተቋሙ ውስጥ ያሉ ሀብት አስመዝጋቢዎች አገልግሎት ሲያቋርጡ ከስራ ክፍሉ ክሊራንስ እንዲወስዱ ያድርጋል። በተቋሙ አገልግሎት ለሚያቋርጡ የሀብት አስመዝጋቢዎች በህጉ መሠረት ዳግም ምዝገባ እንዲያከናውኑ በማድረግ ሰርተፊኬትና ክሊራንስ ይሰጣል ፣ ይህንኑ ለኮሚሽኑ ያሳውቃል፤
- የስነ-ምግባር ጉድለትና የሙስና መከላከል ጥቆማ አቅራቢዎች ሚስጥራዊነት ሊያረጋግጥ የሚችል ስርዓት ይዘረጋል ፣ ስራ ለይ ያውላል ፣ ጥቃት እንዳይደርስባቸው ከለላ እንዲሰጧቸው ሁኔታዎችን ያመቻቻል ፣ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
- በተቋሙ የሰው ኃይል ቅጥር ፣ ደረጃ እድገት ፣ ዘውውር ፣ ሥልጠና ወይም አገልግሎት መረጃ ላይ ሊፈጸም የተሳቡ የሙስና ወንጀል ላይ ጥቆማዎችን ይቀበላል ፣ ድርጊቱ ከመፈጽሙ በፊት የሙስና መከላከል ስራዎችን ይሰራል ፤
- ከሚቀርቡ የስነ-ምግባር ግድፈትና ብልሹ አሠራር ጥቆማዎች በመነሳት ጉዳዩችን ያጣራል ፣ ወደ ወንጀል ምርመራ መግባት ያለበት ሲሆን አመላካች መስረጃዎች በማሰባሰብ ለበላይ አመራሩ በማሳወቅ ለሚመለከተው ክፍል ምርምራ እንዲጣራ ይመራል ፣ የስራ ክፍል ሃላፊዎች ለሚፈጽሟቸው የዲሲፕሊን ጥፋቶች ጥቆማ በመቀበል ደንብ ቁጥር 443/2011 አንቀጽ91 በሚያዘው መሠረትና በተቋሙ በ2012 በተደረገው የአሠራርና የአደረጃጀት ጥናት ሠነድ መሠረት በበላይ አመራሩ ሲወሰን ክስ ይመሰርታል ፣ ክትትል ያደርጋል።
