የወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ ዳይሬክቶሬት

የወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ ዳይሬክቶሬት በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሥር የሚገኝ የሥራ ክፍል ሲሆን በአንድ በተፈፀመ ወንጀል ጠቋሚ ወይም ምስክር ከሆኑ ግለሰቦች የሚቀርብ የሕግ ከለላ ጥያቄን በማጣራት ከለላ ያሰጣል ወይም አያሰጥም ውሳኔዎችን መስጠት፣ የተሰጡ ከለላዎች መፈፀማቸውን መከታተል፣ በወንጀል ጉዳይ ጠቋሚ ወይም ምስክር የሆኑ ግለሰቦች ከሚደርስባቸው ጥቃት እንዲጠበቁና ያለ ስጋት ምስክርነታቸውን በመስጠት አጥፊዎች በሕግ እንዲጠየቁና የሕግ የበላይነት እንዲከበር ማድረግ ከተሰጡት ኃላፊነቶች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

የሥራ ክፍሉን ያግኙ

የሥራ ክፍሉ መሪ

ተረፈ አሰፋ