ከፍትሕ ሚኒስቴር ከፍትሕ ለሁሉም ኢትዮጰያ/ Justice For All-PF Ethiopia/ ጋር በመተባበር ለሚሰራዉ ስራ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ ያገኘዉን ድጋፍ በጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል እና በዳግማዊ ምኒልክ ኮምፐርሄንሲቭ ስፔሻሊዝደ ሆስፒታል የሚገኙትን የፍትሕና እንክብካቤ ማእከላት አገልግሎት ለማሻሻል የሚያግዙ ግብአቶች ርክክብ ግንቦት 28/2017 ዓ.ም ተደርጓል፡፡
በፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታ እና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ጽ/ቤት ኃላፊ መዝሙር ያሬድ ኢትዮጵያና ፈረንሳይ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸዉ ገልጸዉ ድጋፉ ለተለያዩ ጾታዊ ጥቃቶች ተጋላጭ የሆኑትን ሴቶች እና ህጻናት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል፡፡
የዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ተከተል ጥላሁን እንዳሉት ከፍትሕ ለሁሉም ኢትዮጰያ/ Justice For All-PF Ethiopia/ ድጋፉን ከፈረንሳይ ኤምባሲ እንዳገኘ ገልጸዉ ኤምባሲዉ ባለፉት ዓመታት ለሆስፒታሉ የተለያዩ የሰብዓዊ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል፡፡ ዶክተር ተከተል አክለዉም ኤምባሲዉ ሆስፒታሉ የገንዘብ ድጋፍ ከማድረግ ጎን ለጎን የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን እና ለታካሚዎቹ የሚያግዝጉ ቁሳንቁሶችን ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡
የፍትሕ ለሁሉም ኢትዮጰያ/ Justice Forum/ ፕሬዚዳንት ፓስተር ዳንኤል ገ/ስላሴ በበኩላቸው በኢትዮጵ የፈረንሳይ ኤምባሲ የድጋፍ አገልግሎቱን በማኑዋል ዝግጅት፤ በሥልጠናና የተለያዩ ምርምሮችን በማድረግ መጀመሩን ገልጸዉ ኤምባሲዉ እስካሁን ለሰጠዉ ድጋፍ አመስግነዋል፡፡ እስካሁን ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፤ አዲስ አበባ ፖሊስ፤ ፍትሕ ሚኒስቴር እና ጤና ሚኒስቴር ጋር በጋራ መስራታቸዉን ገልጸዉ በቀጣይም ይህ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ ዛሬ የተደረገዉ የግብአት / material/ ድጋፍ በሆስፒታሎቹ የሚገኙት በአንድ ማእከላት (one stop center) ለሚሰጡት የህክምና አገልግሎቶች ጠቀሜታዉ የጎላ መሆኑን ተናግረዉ፣ ባለፉት ዓመታት አብረዋቸዉ የሰሩትን ባለድርሻ አካላት አመስግነዋል፡፡
በመጨረሻም በዳግማዊ ምኒልክ ኮምፐርሄንሲቭ ስፔሻሊዝደ ሆስፒታል የሚገኘዉን የአንድ ማእከል በመጎብኘት የእለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል፡፡