በ2015 ዓ.ም ለተሾሙ ዐቃቢያነ ህግ ስልጠና መስጠት ተጀመረ

Training Commences for Prosecutors Appointed in 2015 E.C

የፍትሕ ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም ለተሾሙ 59 ዐቃቢያነ ሕግ ለሀያ ሶስት ቀናት የሚቆይ ሥልጠና በዛሬዉ እለት መስጠት ጀምሯል፡፡

በፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሃን በሥልጠናዉ መክፈቻ ላይ ተገኝተዉ ባስተላለፉት መልእክት በቅድሚያ ሰልጣኞችን እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ የዐቃቢያነ ሕግ የቅድመ ስራ ሥልጠና በተለያዩ ምክንያቶች በወቅቱ ሳይሰጥ መቆየቱን በመጠቆም ይህንኑ ለማካካስ በቂ ዝግጅት በማድረግ ሰፊ እና ጥልቅ ክህሎት ሊያስጨብጡ የሚችሉ የሥልጠናዉ ርዕሶችን በማካተት መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡

ቀጥለዉም ሰልጣኞች ለአንድ ዓመት ያህል በስራ ላይ የቆያችሁ እንደመሆናችሁ በሥልጠናዉ ወቅት ሞጋችና ጠያቂ በመሆን በንቃት እንደምትሳተፉ እና ከመድረኩ በቂ እውቀት እና ልምድ እንደምትቀስሙ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡

የሥልጠናዉ ካሪኩለም ሲዘጋጅ እዉቀት፤ ክህሎትንና ስነ ምግባርን በማካተት እንደሆነ የገለፁት ሚኒስቴር ዲኤታዉ አንዳንድ ጉዳዮች በቀጥታ ስራ ላይ ላይዉሉ ቢችሉም ነገር ግን የማወቂያ ዘዴዎችን ማወቅ ከእዉቀት በላይ መሆኑን በማመን በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲከታተሉም በአፅንኦት ካሳሰቡ በኋላ ሥልጠናዉን ለማዘጋጀት ተሳትፎ ላደረጉ የፍትሕና ሕግ ምርምር ኢንስቲቲዩት፣ በፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬትና አሰልጣኞችን በማመስገን ንግግራቸዉን ቆጭተዋል፡፡

የፌዴራል ፍትሕና ሕግ ምርምር ኢንስትቲዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘካርያስ ኤርኬሎ በበኩላቸዉ ባለፈዉ ዓመት ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ለዐቃቢያነ ሕግ ሥልጠና መስጠታቸዉን ካነሱ በኋላ አጋጣሚዉም ጥሩ ልምድና ተሞክሮ እንደነበር አስታዉሰዉ ዘንድሮ በአንዳንድ እክሎች ምክንያት ሥልጠናዉ መዘግየቱን ገልፀዋል፡፡

አያይዘዉም ተቋማቸዉ ከሚተግባራቸዉ ዋና ዋና ተግባራት ዉስጥ አንደኛዉ ለፍትሕ አካላት የሚሰጡ ሥልጠናዎች መሆናቸዉን በመግለፅ ይህ ሥልጠናም የዚሁ አንድ አካል መሆኑንና ሥልጠናዉም በርከት ያሉ ርእሶች የሚዳሰሱበት መሆኑን ካስረዱ በኋላ ሰልጣኞችም ልምድ የምትለዋወጡበትና አቅማችሁን የምታጎለብቱበት ከመሆኑም በተጨማሪ ፍትሕ ሴክተሩ የሚወቀስባቸዉ ነገሮችን በመቅረፍ ረገድ የጋራ ጥረት በማድረግ ልንሰራ ይገባል ሲሉ ሰልጣኞች ይህንን ሥልጠና ሲያጠናቅቁም ሰርቲፊኬት እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

ሥልጠናዉ በልዩ ልዩ አዋጆች የተካተቱ ወንጀሎች፣ የስነ-ሥርዓትና የማስረጃ ህጎች ፣ የክርክር ክህሎት እንዲሁም ሙያዊ ስነ ምግባር በሚሉ ሶስት ዋና ዋና ርእሰ ጉዳዮች ተክፈሎ እንደሚሰጥ በፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ሥልጠናና ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸዉ ወርቁ ለሰልጣኞች አብራርተዋል፡፡

በዛሬዉ የመጀመሪያ ቀን ዉሎዉም በልዩ ልዩ አዋጆች የተካተቱ ወንጀሎች ስር በሽብር፣ በሰዉ መነገድና ሰዉን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል፣የሳይበር (የኮምፒዉተር) ወንጀሎች ላይ የሚያተኩረዉን ሥልጠና የሚሰጡት በፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል በሆኑት በአቶ ሀብታሙ ሀይሌ አማካኝነት መሰጠት ተጀምሯል፡፡

Tagged Under: 2015 Amhara amhara region Capacity Building continuing legal education criminal criminal law cybercrime Evidence Law federal human Human Trafficking institute Justice Justice Ministry law legal legal skills Legal Training ministry Procedural Law Professional Ethics Prosecutor Prosecutor training region Research Smuggling Training training curriculum
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች