ባሕላዊ የእርቅ ሥርዓቶች ማኅበራዊ መስተጋብሮችን ሲያሳልጡ የኖሩ እሴቶች ናቸው

Traditional Reconciliation Systems Are Long-Standing Values That Facilitate Social Interaction

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የባሕል ፍርድ ቤቶች እውቅና መስጫ እና የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ታኅሣሥ 21/2018 ዓ.ም አካሂዷል።

በማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ ወቅትም የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኤርምያስ የማነብርሃን የግጭት መፍቻ ባሕሎች ለዘመናት ጥቅም ላይ ይውሉ የነበሩ እሴቶች መኾናቸውን አውስተው፣ የሰዎችን ማኅበራዊ መስተጋብሮች ሲያሳልጡ የኖሩ እሴትች ስለመኾናቸውም ገልጸዋል።

እንደ ሀገር እነዚህን ባሕላዊ የእርቅ ሥርዓቶች ደግፎ እና የሕግ ማዕቀፍ አበጅቶ ሥራ ላይ የማዋል ሥራ አለመከናወኑንም አስታውሰዋል። የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያውን ተከትሎ ግን ባሕላዊ ፍርድ ቤቶች እውቅና ተሰጥቷቸው እንዲሠሩ ልዩ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል።

በአሁኑ ሰዓትም አማራ ክልልን ጨምሮ ሰባት ክልሎች ሕግ አውጥተው ባሕላዊ ፍርድ ቤቶችን እየተጠቀሙ ይገኛሉ ብለዋል። አማራ ክልል ከገጠመው ወቅታዊ የግጭት ሁኔታ በአጭር ጊዜ በመውጣት ይህንን የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀቱ ልዩ እንደሚያደርገውም ገልጸዋል።

ፍትሕ ሚኒስቴር በሁሉም ክልሎች ባካሄደው ጥናት መሠረት ከ80 በመቶ በላይ ሰዎች በባሕል ፍርድ ቤት የመዳኘት ፍላጎት እንዳላቸው ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።

በግጦሽ መሬት፣ በውርስ፣ በፍች፣ እና በመሳሰሉት መንገዶች ከሚከሰቱ አለመግባባቶች ውስጥ 43 በመቶው መፍትሔ የሚያገኙት በባሕላዊ እርቅ ስለመኾኑም ዶክተር ኤርሚያስ ተናግረዋል። ይህም የሚያሳየው የሕዝቡ በባሕላዊ ፍርድ ቤቶች የመዳኘት ፍላጎት ከፍተኛ መኾኑን የሚያሳይ ስለመኾኑ አስረድተዋል።

ባሕላዊ ፍርድ ቤቶች በአማራ ክልል እውቅና ተሰጥቷቸው ሥራ እንዲጀምሩ መደረጉ በወቅቱ የሚታዩ ግጭቶች እንዲፈቱ የራሱ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም አመላክተዋል።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ባሕላዊ የግጭት መፍቻ መንገዶች እንዲስፋፉ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰው ወደፊትም የሚደረገውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

የዜና ምንጭ፡- አመራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

Tagged Under: act action and healthcare administration and control authority conciliation decree Ethiopian Social Rehabilitation and Development Fund financial system safety and soundness harmonized commodity description and coding system judicial law legal legislation medicine and healthcare administration and control authority medicine and healthcare administration and control proclamation no. 661/2009 ministry of labor and social affairs ministry of labour and social affairs Policy proclamation reconciliation Regulation social standing statute system systems traditional value values
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች