በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር የመንግስት ህግና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ ከአለምአቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) በኢትዮጵያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊ (Chief of Mission for Ethiopia) የተከበሩ ሚስ አቢባቱ ዋኔ ጋር ተወያዩ

State Minister of Government Law and Justice Services Sector, His Excellency Ato Belayhun Yirga, Discusses with the IOM Ethiopia Chief of Mission, Her Excellency Ms. Abibatou Wane

በኢትዮጵያ በሰው መነገድና ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎችን በመከላከል፣ ተጎጂዎችን በመጠበቅ፣ ወንጀል ፈጻሚዎችን ለሕግ በማቅረብ፣ መደበኛ ፍልሰትን በማሳለጥ የሚገኙትን ጥቅሞች በአግባቡ ለመጠቀም በአጠቃላይ የተሻለ የፍልሰት አስተዳደርን በማስፈን፤ ለዚህም ሀገራዊና አለምአቀፋዊ ትብብርን በማጠናከር ዙሪያ የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ ከአለምአቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በኢትዮጵያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊ የተከበሩ ሚስ አቢባቱ ዋኔና ልዑካቸው ጋር ዛሬ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ውይይት አድርገዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ሀገራችን የተሻለ የፍልሰት አስተዳደር ለመዘርጋት በምታደርገው ጥረት ውስጥ ብሔራዊ የፍልሰት ትብብር ጥምረት ሰብሳቢ የሆነው ፍትሕ ሚኒስቴርና የአለምአቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በቅርበት በትብብር እየሰሩ እንደሆነ ገልፀው ይህንንም ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በቅርቡ የሁለትዮሽ የአጋርነት ስምምነት ተፈራርመን ወደስራ ገብተናል ብለዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም ወንጀሎቹን የመከላከል፣ የመቆጣጠርና የተሻለ የፍልሰት አስተዳደር የመዘርጋት ኃላፊነት የአለምአቀፍ ትብብርን የሚጠይቅ በመሆኑ ከዜጎቻችን መተላለፊያና መዳረሻ ሀገራት ጋር ውይይቶችን በማድረግ፤ ከላይ ከተጠቀሱት ወንጀሎች አንጻር የተጋላጭነት ካርታ ማዘጋጀትን ጨምሮ የሀገራችንን የፍልሰት መግለጫ (Migration Profile) በማሻሻል፤ የወንጀሎቹ የተጠያቂነት ስርዓት በመዘርጋት፤ ስለወንጀሎቹ በቀላሉ መረጃ ለመለዋወጥ ዓላማ ሀገራዊ አጭር የስልክ ጥሪ (National Hotline Service) በማዘጋጀትና ተግባራዊ በማድረግ፤ በክልሎች ክልላዊ የፍልሰት ምክር ቤትና የትብብር ጥምረት አደረጃጀቶች እንዲቋቋሙና እንዲጠናከሩ በማድረግና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ከድርጅቱ ጋር በጋራ ለመሥራት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል፡፡

የአለምአቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በኢትዮጵያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊ የተከበሩ ሚስ አቢባቱ ዋኔ በበኩላቸው ከፍልሰት ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ በፍትሕ ሚኒስቴርና ሌሎች ተቋማት በቅንጅት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አድንቀው ሀገሪቱ በምታካሂደው በሁሉም የፍልሰት አስተዳደር ዘርፍ ከብሔራዊ የፍልሰት የትብብር ጥምረትና ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በቅርበት ለመሥራትና ድጋፍ ለማድረግ ድርጅታቸው ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፡፡

በመቀጠልም ኃላፊዋ በረቂቅ ደረጃ የሚገኙት የፍልሰት ፖሊሲ፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃ አዋጅና የሰው መነገድና ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎች ጥበቃና መልሶ ማቋቋም ፈንድ ደንብ ስላሉበት ደረጃ ጥያቄ አንስተው ምላሽ የተሰጣቸው ሲሆን ጸድቀው ወደስራ ቢገቡ ያላቸውን ጠቀሜታም ገልፀዋል፡፡

Tagged Under: accountability mechanisms agreement belayhun yirga bilateral Bilateral Agreement border border smuggling Capacity Building Cooperation human Human Trafficking international International Cooperation iom Justice Ministry legal framework management Migration Migration Management Migration Policy National policy drafting Refugee Protection Smuggling state minister trafficking
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች