በስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ዙሪያ ያሉ አሰራሮችንና በማህበረሰቡ ብሎም በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረዉን ተጽእኖ በጥናት በመለየት እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚገባ ተገለፀ

Need to Address Problems in Sports Betting by Studying its Procedures and Impact on Society and National Economy

ይህ የተባለው ፍትሕ ሚኒስቴር፣ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር፣ ገቢዎች ሚኒስቴር፣ ገንዘብ ሚኒስቴር ፣ ሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲሁም ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውስ ውስጥ እየከተተ ነው፣ የወጣቶችን እና ሕፃናትን ህይወት እያበላሸ ነው የሚሉ ቅሬታዎችን መነሻ በማድረግ በፍትሕ ሚኒስቴር አስተባባሪነት ችግሮችን ለመቅረፍና ሕጋዊ አሠራርን ለማስፈን ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

ውይይቱን በንግግር የከፈቱት በፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ አቶ አለምአንተ አግደው የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) በኢትዮጵያ በሕግ የተፈቀደና አጫዋች ድርጅቶችም በዘርፉ የተሰማሩ ቢሆንም በአንድ በኩል ሕፃናትን ጨምሮ ማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውስ ውስጥ እየከተተ ነው በሌላ በኩል ደግሞ ለዜጎች የስራ እድል እፈጠረና ለሀገርም ገቢም ያስገኛል ይገኛል የሚሉ ሃሳቦች ይነሳሉ በእነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊና ጥልቅ የሆነ ጥናት በማካሄድ የስፖርት ውርርዱ አስፈላጊ ነው ወይም አይደለም የሚለዉን በጥናት ለይተን ተገቢ የሆነ እርምጃ መውሰድ ይገባል በማለት ተናግረዋል፡፡

በፍትሕ ሚኒስቴር በመንግሥት ሕግ እና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ የፌዴራል ሕጎች ተፈጻሚነት መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ትብለጥ ቡሽራ በስፖርት ውርርድ ዙሪያ በተደረገ ዳሰሳ የተለዩ ችግሮች እና የመፍትሄ ሀሳቦችን ለውይይቱ ታዳሚዎች አቅርበዋል፡፡

የቀረበዉን የዳሰሳ ጥናት መነሻ በማድረግም የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) እንደ ሀገር እያሳረፈ ባለው ተፅዕኖ ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት ከተደረገ በኋላ ምክክር መድረኩን የመሩት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አለምአንተ አግደው በማጠቃለያ መልዕክታቸው በጉዳዩ ላይ መፍትሄ ለመስጠት ይቻል ዘንድ በፍትሕ ሚኒስቴር አስተባባሪነት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ አመራሮች በአብይ ኮሚቴነት የሚመሩት የቴክኒካል ቡድን ተዋቅሮ ጥልቅ የሆነ ሀገር አቀፍ ጥናት ማካሄድ እንደሚገባ የገለጹ ሲሆን በዚህም ላይ ከስምምነት ላይ ተደርሶ የምክክር መድረኩ ተጠናቋል፡፡

Tagged Under: administration affairs betting economic impact assessment finance gambling gambling regulation legal framework lottery ministry ministry of culture and sports Ministry of Finance ministry of revenue ministry of women and social affairs National national lottery administration policy recommendations Regulation Revenue social social impact assessment sports sports betting Stakeholder Consultation technical committee women
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች