በፍትህ ሚኒስቴር የመንግስት ህግና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ የ2017 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀምን በዛሬዉ እለት ገመገመ

Ministry of Justice's Government Law and Justice Services Sector Reviews Nine-Month Performance for 2017 Budget Year

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀምን የሕግና ፍትሕ ማሻሻያ ስራዎች ዉጤታማነትን ከማሳደግ፣ የሶስት አመቱን የፍትሕ ትራንስፎርሜሽን እቅድ እና የስነ-ምግባር የድርጊት መርሃ ግብርን በተመለከቱ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ በመመስረት ገምግሟል፡፡

የ2017 የበጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በዘርፉ በርካታ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን ለአብነትም የሕግ ጥናት ማርቀቅና ማጠቃለል ስራዎችን በተመለከተ የስራ ክፍሉ ከሕግ ጥናት ስራዎች ጋር በዘጠኝ ወራት ዉስጥ 8 ጥናቶችን ማካሄዱንና ፣ሕግ ማርቀቅን በተመለከተም 13 ህጎች የተረቀቁ ሲሆን በተጨማሪም 32 ህጎችን በማርቀቅ ሂደት ለተቋማት ድጋፍ መደረጉንና በ192 ረቂቅ ህጎች ላይ ደግሞ የዕርምት ስራ እና ሌሎች ተግባራት መከናወናቸው ተገልፆል፡፡

በሀግ ጉዳዮች ዓለም ዓቀፍ ትብብርን ማሳደግ ጋር በተያያዘ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን በተመለከተ ከቻይና ጋር ሁለት እንዲሁም ከብራዚል ጋር አንድ የተካሄደ ሲሆን በተጨማሪም ከሌሎች አገራት ጋር መሰል ግንኙነቶች እየተደረጉ እንደሚገኙ የተገልዖል፡፡

ከበይነ መንግስታት ስምምነቶች ጋር በተገናኘ እንዲሁ አገራችን የሄግ አፕስታይል ኮንቬንሽን አባል እንድትሆን ለማድረግና የዓለም ዓቀፍ የግልግል ዳኝነት ድርጅት መገኛ ለማድረግ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን እና በአሳልፎ መስጠት፣ ፍርደኞችን ማስተላለፍና በሌሎች ተግባራት ሰፋ ያሉ ስራዎች መከናወናቸው ተጠቁሟል።

ከፍትሃብሄር ፍትሕ አስተዳደር ተግባራት ጋር በተገናኘም በስራ ክፍሉ ከተያዙና ከክርክር ጋር የተያያዙ ከፍርድ ቤት ዉጭ ባሉ አማራጭ አለመግባባት መፍቻ መንገዶች ማለትም ከድርድርና የግልግል ዳኝነት፣ የሕግ ምክር ዉል ረቂቅ፣ የኦዲት ግኝት መመርመር ጋር በተገነኘ በርካታ ተግባራት መከናወናቸዉ ተገልፆል፡፡

ለአብነትም ቀጥታ ክስ መዛግብት በተመለከተ 281 መዛግብት ቀርበዉ 123 መዛግብት ዉሳኔ ያገኙ ሲሆን እነዚህ መዛግብት ነፃ የሕግ ድጋፍ የሚሰጡባቸዉ በመሆናቸዉ የሴቶችን የአካል ጉዳተኞችንና የአረጋዉያንን መብት ከማስከበር በተጨማሪ ተቋማት ሊያወጧቸዉ የሚቸሉትን በርካታ የገንዘብ ቁጥር ያለዉን ሃብት ማዳን መቻሉ ተገልዖል፤ ጉዳዮችን በአማራጭ አለመግባባት መፍቻ መንገዶች መቋጨት በተመለከተም 43 ጉዳዮች ቀርበዉ 33ቱን በስምምነት መጨረስ የተቻለ ሲሆን በዉጭ አገራት በግልግል ዳኝነት ከሚታዩ አራት መዛግብት ዉስጥ ደግሞ ሁለት መዛግብት ዉሳኔ አግኝተዋል፡፡

በጥቅሉ ለዘርፉ ተጠሪ የሆኑ ሌሎች የስራ ክፍሎች አማኝነት እንዲሁ በዘጠኝ ወራት በርካታ ተግባራት መከናወናቸዉን በስራ ክፍል ሃላፊዎቹ በቀረቡ ሪፖርቶች ተመላክቷል፡፡

በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ ሀሳብ፣አስተያየትና ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን በፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ እንዲሁም በስራ ክፍል ሃላፊዎች አማካኝነት ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በመጨረሻም በዘርፉ ከባለሙያ ምዘና እና ስነ-ምግባር ጉዳይ፤ በተቋሙ የለሙ ቴክኖሎጂዎችን ከመጠቀም፤ የተከለሰውን የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተግባራዊ ከማድረግ፤ ተቋማዊ የአሰራ ስርአቶችን ከማወቅ እና መተግበር፤ ከሰው ኃይል አጠቃቀም፤ ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋር በቅንጅት እና በባለቤትነት ከመሥራት እንዲሁም የክትትል እና ድጋፍ ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠልን አሰመልክቶ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በሰጡት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ የግምገማ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

Tagged Under: alternative dispute resolution (adr) Arbitration Asset Recovery Bilateral Agreements Budget budget year 2017 Capacity Building code of conduct disability rights drafting legislation elderly rights Ethiopian Ministry of Justice Government hague convention international commercial arbitration International Cooperation Justice justice transformation plan law Legal Aid Legal Reform legal research Mediation ministry nine-month performance review Performance Evaluation Services Women's Rights year
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች