ፍትሕ ሚኒስቴር በሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ የተለያዩ ሀገራትን በመደገፍ ከሚታወቀው የአሜሪካ ጓደኛሞች አገልግሎት ኮሚቴ (the American Friends Service Committee (AFSC) ጋር በሽግግር ፍትሕ ትግባራ ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የሚያሰችል መግባቢያ ተፈርሟ፡፡
ተቋማቱ በዚህ የመግባቢያ ሰነዱ ሁለቱም ተቋማት በሀገራዊ የሰላም ግንባታ እና እርቅ ዙሪያ በተናጠል ከሚያከናውኑት ተግባራት በተጨማሪ በጋራ ሊሰሩ በሚችሉባቸው የተመረጡ የትብብር መስኮች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል ፡፡ በዚህም መሠረት ሁለቱ ተቋት በባለሙያዎች ሥልጠና፣ ጥናት እና ምርምር፣ ህዝባዊ ውይይትን ማስተባበር፣ በሕግ እና ፖሊሲ ዝግጅት፣ እና መሰል ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመሥራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ፍትሕ ሚኒስቴርን በመወከል በሰነዱ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ ሲሆኑ በአሜሪካ ጓደኛሞች አገልግሎት ኮሚቴ በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ የኮሚቴው ዳይሬክተር የሆኑት ሚስተር ሞሰስ ቻሲ ናቸው፡፡