የፍትሕ ሚኒስቴር ስርዓተ ፆታን ያማከለ የህግ ማርቀቅ ቴክኒኮች ላይ ስልጠና ሰጠ

Ministry of Justice Provides Training on Gender-Sensitive Legal Drafting Techniques

ሥልጠናው የተሰጠው በፍትሕ ሚኒስቴር በተዘጋጀ የስርዓተ-ጾታ ማካተቻ የአሠራር ማኑዋል ላይ ሲሆን ለሁለት ቀናት በቆየው ሥልጠና ላይ ከ11 ክልሎች በሕግ ማርቀቅ የስራ ክፍሎች ላይ የሚሰሩ ዐቃብያነ ህጎች ተሳትፈዋል፡፡

የሥልጠና መድረኩ በሕግ ማርቀቅ ሂደት የስርዓተ- ጾታ አካታችነት በጠቅላላ የሕግ ማርቀቅ ሂደት ውስጥ የሚካተት መሆኑን ግንዛቤ የተፈጠረበት እዲሁም የስርዓተ- ጾታ አካታችነት ልዩ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑ የተመላከተበት ነው ፡፡

ይኸውም ሴቶች እና ወንዶች እኩል የሆነ የመብት ጥበቃ እንዲያገኙ ፤ በማኅበራዊ ፣በኢኮኖሚ እና በፖለቲካው ዘርፍ የተሳትፎ እድል እንዲያገኙና እንዲጠቀሙ ለማስቻል ፤ ከስርዓተ- ጾታ እኩልነት ሞዴል ስትራቴጂዎች ውስጥ ሴትና ወንድ በመርህ ደረጃ እኩል ናቸው ነገር ግን ልዩ ፍላጎት ታሳቢ ሊደረግ ይገባል የሚለው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው መሆኑ ተገልፆል፡፡

የአሠራር ማኑዋሉ ላይ በተቀመጠው መሠረት፣ እቅድ ሲዘጋጅ እና ሲተገበር በሴቶች እና በወንዶች ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ ላይ ጥናት/ዳሰሳ/ በማድረግ መገምገም ፣ ተሳትፎን ማረጋገጥ፣ ልዩ ፍላጎትን ታሳቢ ማድረግ እና የስርዓተ-ጾታ ማካተቻ ሰነድ ማዘጋጀት በሕግ ማርቀቅ ሂደት የስርዓተ ጾታ አካታችነት ስልቶች /ተግባራት/ ናቸው፡፡

በዚህም መሠረት ክልሎች በሕግ ማርቀቅ ሂደት የስርዓተ- ጾታ አካታችነትን በእቅድ አካተው እንዲሰሩ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡ በሥልጠናው ላይ በተነሱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊዎች ሃሳብና ጥያቄዎችን አንስተው በአሰልጣኞች አማካኝነት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው የሥልጠና መድረኩ ተጠናቋል፡፡

Tagged Under: building capacity civil liberties development drafting Equality fundamental rights gender Gender Equality gender inclusion gender mainstreaming gender-sensitive Human Rights Impact Assessment inclusion legal Legal Capacity Building legislative legislative drafting mainstreaming Policy Policy Development Training training workshop Women's Rights
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች