የአንድ ማዕከላት የአገልግሎት አሰጣጥ የምዘና ሪፖርት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት ተካሄደ

A discussion was held with stakeholders regarding the service delivery assessment report of a One-Stop Center's.

በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚፈጸም ጥቃት መከላከል እና ምላሽ መስጠት ብሄራዊ አስተባባሪ አካል አስተባባሪነት የተካሄደ ጥናትን መሰረት በማድረግ የቀረቡ አገራዊ እና ክልላዊ የአንድ ማዕከላት የአገልግሎት አሰጣጥ የምዘና ሪፖርት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት ተካሂዷል፡፡

የምዘናዉ ዋና ዓላማ ማዕከላቱ የተጎጂዎችን መብትና ፍላጎቶችን በማገናዘብ ደረጃቸዉን የጠበቀ ሁሉን ዓቀፍ አገልግሎቶች እየሰጡ መሆናቸዉን ለመመዘን እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ምዘናዉ የተካሄደዉ በ12 ክልሎች እና 2 ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ ካሉ 92 ማዕከላት ውስጥ በ67ቱ ላይ ሲሆን የማዕከላቱ አደረጃጀትና ምቹነት፤የሰዉ ኃይል ስብጥር፤ማዕከላቱ የሚሰጡት አገልግሎት፤የባለጉዳይ አያያዝና የመረጃ አደረጃጀት እና ቅንጅታዊ አሠራር እንዲሁም የቅብብሎሽ እና የንብረት አያያዝ ሥርዓት ዋነኛ የመመዘኛ መስፈርቶች እንደነበሩም በጥናት ቡድኑ ሪፖርት ላይ ተመላክቷል ፡፡

በሪፖርቱ የተመዘገቡ የተሻሉ አፈጻጸሞችና የታዩ ክፍተቶች ተለይተዉ የቀረቡ ሲሆን፣ የሚመለከታቸው መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ባለድርሻ አካላት ድጋፍና ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ እንደ ሀገር ወጥ የሆነ የአሠራር እና የመረጃ ሥርዓት እንዲኖር በቀጣይ መሥራት እንደሚገባ ምክረ-ሀሳብ ቀርቧል፡፡

በመጨረሻም ምዘናው ከተካሄደባቸው 67 ማዕከላት መካከል ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 3 የአንድ ማዕከላት እና የምዘና ሥራዉን ላከናወኑ ባለሙያዎች እዉቅና የተሰጠ ሲሆን፤ በውይይት መድረኩ ላይ ከፌደራል ባለድርሻ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች እና ከክልል ፍትሕ ቢሮ፣ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ፣ ከአንድ ማዕከላትና አጋር አካላት የተወከሉ የሥራ ሃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Tagged Under: accreditation service fee african charter on the rights and welfare of the child assessment center Convention on the Rights of the Child convention on the rights of the child (crc) decentralized service delivery delivery Discussion health service delivery integrated service delivery justice service delivery live old one one stop center one-stop One-Stop Service port Public Service Delivery report Service Service Delivery service delivery improvement service delivery standards sme stakeholder stakeholders un convention on the rights of the child vice
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች