ፍትሕ ሚኒስቴር ከወንጀል መከላከል ጋር በተያያዘ በሀገራችን እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለተለያዩ ሀገራት እና አለማቀፍ ተቋማት ተወካዮች አቀረበ

Ministry of Justice Presents Ethiopia's Efforts in Crime Prevention to Representatives of Various Countries and International Organizations

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 15ኛው የወንጀል መከላከልና የወንጀል ፍትሕ ኮንግረስ (15th UN Congress on Crime Prevention and Criminal Justice) የአፍሪካ አህጉር የቅድመ ዝግጅት ስብሰባ እ.ኤ.አ ከኤፕሪል 8-10 ቀን 2025 በአዲስ አበባ እየተካሔደ ይገኛል፡፡

በዚህ መድረክ ላይ በፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ የተመራ ቡድን በሀገራችን ከወንጀል መከላከል ጋር በተያያዘ ፖሊሲና ስትራቴጂ ከመቅረጽ፣ ህጎችን ከማውጣት እና ከመተግበር ጀምሮ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እና በቀጣይ ሊሰሩ በታቀዱ ተግባራት ዙሪያ ለተለያዩ ሀገራት እና አለማቀፍ ተቋማት ተወካዮች በማቅረብ የልምድ ልውውጥ አድርጓል፡፡

Tagged Under: addis ababa Capacity Building Crime Crime Prevention criminal Criminal Justice enforcement Experience Sharing international international organizations judicial Judicial System Justice law Law Enforcement legal Legal Reform organizations Police Policy prevention reform Security Strategy system Technical Assistance
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች