ፀባቸው በግልጽ ተለይቶ ባልታወቀ ምክንያት ከሟች ጋር ሲጨቃጨቅ ቆይቶ ይዞት በነበረው ጩቤ በመውጋት ሰው የገደለው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ

Man Sentenced to Rigorous Imprisonment for Fatally Stabbing Another Following an Argument with an Unclear Cause

ዮርዳኖስ ተፈሪ የተባለው ተከሳሽ ሆን ብሎ ሰውን ለመግደል በማሰብ መስከረም 5 ቀን 2015 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 5፡40 ሰዓት አካባቢ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ባርጌቾ ሱቅ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሟች ሳሙኤል ጅሃድ ጋር በግልጽ ተለይቶ ባልታወቀ ምክንያት ከሟች ጋር ቆሞ ሲጨቃጨቅ ከቆየ በኋላ ይዞት በነበረው ስለት ባለው ጩቤ ደጋግሞ ሟችን የግራ ደረቱን፣ የግራ ጡቱ ላይ እና የግራ ታፋው ላይ በመውጋት በደረሰበት ጉዳት ወዲያው ህይወቱ ያለፈ በመሆኑ በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 539/1/ሀ/ መሠረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት በፈፀመው ከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን በተሰጠው መሠረት ተከሳሽ የመከላከያ ምስክር አቅርቦ ያሰማ ቢሆንም በዐቃቤ ሕግ የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ምክንያት ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት የቅጣት ውሳኔ በማሳረፍ በ18 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኗል፡፡

Tagged Under: conviction • criminalcode1996 • federalhighcourt • felony • Homicide • imprisonment • legalcase • lidetadistrictcourt • manslaughter • Murder • rigorousimprisonment • sentence • Stabbing
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች