ባለቤቱን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ

Man Sentenced to Life Imprisonment for the Gruesome Murder of His Wife

ፀሃዬ ቦጋለ በየነ የተባለ ተከሳሽ ከ27/12/2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 5፡00 እስከ 28/12/2014 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡30 ድረስ ባለው ጊዜ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አርሴማ ፀበል አከባቢ ባለቤቱ የነበረችውን ሟች ወንበር ላይ ተቀምጣ እያለ ሳታየው ከኃላዋ በመምጣት በሊጥ ማዳመጫ ዱላ ማጅራትዋን በመምታት እራስዋ እንድትስት ካደረገ በኃላ እዛው ትቷት ከቤት ወጥቶ በመሄድና ከተወሰነ ሰዓታት በኃላ ተመልሶ በመምጣት ሟች እራስዋን ስታ ከወደቀችበት መሬት ለመሬት በመጎተት እቤት ውስጥ ወደ እሚገኘው መታጠቢያ ቤት በማስገባት አንድ እግሯን ከዳሌዋ ጀምሮ በመቁረጥና ሙሉ የእግሯን ስጋ አጥንትዋ ባዶ እስኪሆን ድረስ መልምሎ በማውጣት ስጋዋን አድቅቆ በመክተፍና በመቆራረጥ ሽንት ቤት ውስጥ በመጨመር የቆረጠው እግሯ ለሁለት በመስበርና በፌስታል በመቋጠር ፀጉሯን በመቀስ በመቁረጥ ቀሪ አስከሬንዋ ላይ ጨርቅና የተለያየ መዘፍዘፊያ በመጫን እዛው መታጠቢያ ቤት ውስጥ በማስቀመጥ እስከ 30/12/2014 ዓ.ም ድረስ ምንም እንዳልተፈጠረ እቤት ውስጥ እያደረ ከቆየ በኃላ ከ1/13/2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 16/1/2015 ዓ.ም ድረስ ቤቱን ዘግቶ በመሰወሩ ምክንያት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በሴቶችና ህጻናት ላይ ሚፈፀሙ ወንጀሎች ዓ/ሕግ ዳይሬክቶሬት በወ/ሕ/አ 539/1/ሀ መሠረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዓ/ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኃላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም የመከላከያ ማስረጃ አቅርቦ የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በ28/10/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ሰጥቱዋል፡፡

Tagged Under: 2014 • 2016 • ababa • addis • addis ababa • brutal murder • Capital • capital punishment • conviction • Criminal Case • domestic • Domestic Violence • Federal High Court • femicide • forensic evidence • imprisonment • lideta district • life • life imprisonment • Murder • police investigation • punishment • Sentencing • violence • wife • wife murder
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች