የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባ ከፌዴራል እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች ጋር የወንጀል ፍትሕ አሰተዳደርን ውጤታማነት ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ የወንጀል ምርመራ፣ ክስ እና ክርክር ስራዎች ውጤታማነትን ለማሳደግ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በተፈረመው መግባቢያ ሰነድ መሰረት ለማከናወን በእቅድ የተያዙ ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በውይይቱ የወንጀል ምርመራ እና ክስ ስራዎች የሚመሩበት የጋራ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋቱ የመዛግብት ቅልጥፍና፣ ጥራት እና ውጤታማነት ማሳደግ የተቻለበት ውጤት የተገኘበት አበረታች ውጤት የተገኘበት መሆኑ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም የተጀምረውን ጠንካራ ቅንጅታዊ ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል፤ በጋራ እና ከሌሎች ተቋማት ጋር የሚደረጉ የመረጃ ልውውጥ ተግባራትን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማዘመን፤ የመርማሪዎችንና የዐቃብያነ ሕግን አቅም የሚያጎለብት ስልጠናዎችን መስጠት እንዲሁም የጋራ ክትትል፣ ድጋፍና ተጠያቂነት ስርዓትን ማጠናከር እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡