ተከሳሽ የሱፍ ሙህዬ ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ደመካ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በግምት ከቀኑ 8፡30 ሲሆን በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 627/1/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ እድሜዋ 11 ዓመት ከ8 ወር የሆነችን ህፃን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል ፍ/ቤት ቀርቧል፡፡
የክስ ዝርዝሩ እንደሚያስረዳው የህፃኗ እናት በተከሳሽ ቤት በተመላላሽ ሰራተኝነት የምትሰራ ሲሆን ህፃኗን ይዛት የምትሄድ ከመሆኑም በተጨማሪ እናቷ በሌለችበትም ጊዜም በግለሰቡ ቤት ትላላካለች በእለቱም በተከሳሽ ቤት ውስጥ TV እያየች በተኛችበት በግምት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት አካባቢ የግብረስጋ ግንኑነት የፈጸመባት እና ክብረ ንጽህናዋ እንዲገረሰስ ያደረገ በመሆኑ ዐቃቤ ሕግ በ1996 የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 627/1/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ሕፃናት ልጆች ላይ የሚፈጸም የግብረ-ስጋ ድፍረት በደል ወንጀል ክስ መስርቶበታል፡፡
ተከሳሽም ፍ/ቤት ቀርቦ ዐቃቤ ሕግ የተከሳሽን ጥፋተኛነት ያስረዳሉ ያላቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃናዎች በማቅረብ የተከራከረ ሲሆን ተከሳሽ እንዲከራከር ብይን ቢሰጠውም ጥፋቱን ማስተባበል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱም ጥፋተኛ ብሎታል፡፡
በመጨረሻም የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ 7ኛ ወንጀል ችሎት የቅጣት ማክበጃ እና ማቅለያ ሁኔታዎችን በማየት ተከሳሹ በ14 ዓመት ከ4 ወር ፅኑ እስርት እንዲቀጣ ሲል ወስኖበታል፡፡