4 ዓመት የሆነው ወንድ ህጻን ልጅ ከመኖሪያ ቤቱ ይዛ የተሰወረች የቤት ሰራተኛ በፅኑ እስራት ተቀጣች

Housemaid Sentenced to Rigorous Imprisonment for Kidnapping a 4-Year-Old Boy

መልካም ጌታቸው አላምሬ የተባለች ተከሳሽ በ18/8/2015 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 10፡00 ሲሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አዲስ አበባ ኮንደሚኒየም እየተባለ በሚጠራው ሰፈር በቤት ሠራተኛነት ተቀጥራ ስትሰራበት ከነበረው መኖሪያ ቤት የ4 ዓመት የሆነው ወንድ ህጻን ልጅ ከመኖሪያ ቤቱ ይዛ በመሰወር ለህፃኑ ወላጅ እናት ብር 25000 (ሃያ አምስት ሺህ) ካላመጣሽ ልጅሽን አታገኝም በማለት ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅን በመጥለፋ ምክንያት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በሴቶችና ህጻናት ላይ ሚፈፀሙ ወንጀሎች ዓ/ሕግ ዳይሬክቶሬት በወ/ሕ/አ 590/1/ለ እና 2/መ/ መሠረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ልዩ ልዩ ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦባት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዓ/ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኃላ ተከሳሽ እንድትከላከል ብይን ቢሰጥም ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ በማቅረብ የቀረበባትን ክስ ልትከላከል ባለመቻሏ ፍ/ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በ27/10/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ በ6 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ውሳኔ ሰቷል፡፡

Tagged Under: Abduction • addis ababa • child • Child Abduction • child trafficking • conviction • court • Criminal Case • Criminal Code • district • domestic • Domestic Worker • federal • Federal High Court • federal supreme court • high • imprisonment • Kidnapping • lideta • lideta district court • police commission • rigorous • Rigorous Imprisonment • sentence • worker
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች