እግድ ባለበት የመሬት ይዞታ ላይ ካርታ ሰርቶ ለመስጠት 1 ሚሊዮን 500 ሺ ብር ጉቦ በተቀበለና ተጨማሪ 2 ሚሊዮን ብር ጉቦ በጠየቀው የቂርቆስ ክ/ከተማ የመሬት ልማት አስተዳደር የሊዝ ውል ባለሙያና ተባባሪው ላይ ከባድ የሙስና ወንጀልና ህ-ወጥ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ክስ ተመሰረተ

Heavy Corruption and Money Laundering Charges Filed Against Kirkos Sub-City Land Development Administration Lease Expert and Accomplice for Accepting 1.5 Million Birr Bribe and Demanding Additional 2 Million Birr for Issuing Map on Restricted Land

በኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ እግድ ባለበት የመሬት ይዞታ ላይ ካርታ ሰርቶ ለመስጠት 1 ሚሊዮን 500 ሺ ብር ጉቦ ክፈለኝ ብሎ በተቀበለና ተጨማሪ ገንዘብ ያስፈልጋል በማለት 2 ሚሊዮን ብር እንዲከፍል ጉቦ በጠየቀው የቂርቆስ ክ/ከተማ የመሬት ልማት አስተዳደር የሊዝ ውል ባለሙያ አቶ ፋሲል አወቀና ተባባሪው ላይ ከባድ የሙስና ወንጀልና ህ-ወጥ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ክስ ክስ መሰረተባቸው፡፡

የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሾች 1ኛ አቶ ፋሲል አወቀ በቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ስር የሊዝ ውል ባለሙያ፣ 2ኛ ማሲን ሮቤ በግሉ የሚሰራ ሲሆኑ፣ ተከሳሾች የእያንዳንዳቸው የተሳትፎ ደረጃ ተጠቅሶ በዐቃቤ ሕግ ሶስት ክሶች ተመስርቶባቸዋል፡፡

የዐቃቤ ሕግ 1ኛ ክስ በ1ኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበ ሲሆን ተከሳሹ በቂርቆስ ክ/ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ውስጥ የሊዝ ውል ባለሙያ ሆኖ በሚሰራበት ወቅት በሃላፊነቱ ወይም በስራ ግዴታው ማድረግ የማይገባውን ለማድረግ በማሰብ ሀምሌ 3 ቀን 2014 ዓ/ም የመሬት ይዞታ ስመ-ንብረት እንዲዞርለት ተከሳሹ ወደሚሰራበት ቢሮ የሄደውን ባለጉዳይ በይዞታው ላይ እግድ እንዳለ ካረጋገጠ በኋላ ካርታው ተሰርቶ እንዲጠብቅህ 1 ሚሊዮን 500 ሺ ብር ክፈለኝ በማለት ገንዘብ በመጠየቅ የተጠቀሰውን ብር በስሙ በሚንቀሳቀሱ የሂሳብ ቁጥሮች ገቢ እንዲደረግለት ካደረገ በኋላ ተከሳሹ ተጨማሪ ገንዘብ ያስፈልጋል በማለት ባለጉዳዩን 2 ሚሊዮን ብር እንዲከፍል የጠየቀ በመሆኑ በፈፀመው ጉቦ መጠየቅና መቀበል ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል፡፡

በተያያዘም በዚሁ ተከሻሽ ላይ በቀረበ 2ኛ ክስ ንብረቱ የወንጀል ፍሬ መሆኑን እያወቀ የንብረቱን ህገ-ወጥ ምንጭ ለመደበቅና ከወንጀል ተጠያቂነት ለማምለጥ አስቦ ከላይ በ1ኛ ክስ በተጠቀሰው ወንጀል አማካኝነት ያገኘውን ብር ሀምሌ 6 ቀን 2014 ዓ/ም ለ2ኛ ተከሳሽ ያስተላለፈ በመሆኑ በፈጸመው በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።

3ኛ ክስ በ2ኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበ ሲሆን ተከሳሹ ንብረቱ የወንጀል ፍሬ መሆኑን እያወቀ ከላይ በ1ኛ ክስ በተጠቀሰው ወንጀል አማካኝነት 1ኛ ተከሳሽ ያገኘውን ብር 1 ሚሊዮን 500 ሺ ብር ሀምሌ 6 ቀን 2014 ዓ/ም ከ1ኛ ተከሳሽ ተረክቦ የተጠቀመ በመሆኑ በፈጸመው በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።

ጉዳዩን የቀረበለት የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የጸረ-ሙስና ወንጀል ችሎት ጉዳዮች ተከሳሾች በተከሰሱበት ክስ መቃወሚያ እንዲያቀርቡ ለጥር 8 ቀን 2015 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Tagged Under: 2 million birr • 2014 • 2015 • administration • bribery • Corruption • Criminal Charges • development • ethiopian federal attorney general • Federal High Court • Financial Crime • july 3 • July 6 • kirkos • kirkos sub-city • land • lideta district • Money Laundering • property crime • sub-city
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች