የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ ከአልጀሪያ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጋር በአልጀሪያ ዋና ከተማ አልጀርስ ተገናኝተው በሁለቱ ሀገራት መካከል በፍትሕ ዘርፍ ያለውን ትብብር እና ቅንጅት የበለጠ ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ ወቅት ሁለቱም አመራሮች ቀጣይ በፍትሕ ዘርፍ ያለውን ግንኙነት ወደተሻለ ደረጃ ማሳደግ የሚቻልባቸውን ጉዳዮች አንስተው ተወያይተዋል።
ክቡር አቶ በላሁን ይርጋ ከአልጀሪያ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር በተጨማሪ ከፍትሕ ሞድረናይዜሽን ተቋም፣/justice modernization directorate General/ የህግና ዳኝነት ጥናት ማዕከል / Legal and Judicial research center/ ከዳኝነት ጉዳይ ተቋም/Judicial affairs directorate General/, የማረሚያ ቤት ሰራተኞት ማሰልጠኛ ተቋም /National School for prison administration staff / እና የማጂስትሬሲ ከፍተኛ ትምህርት ቤት /Higher school of magistracy/ አመራሮች ጋር ተገናኝተው በሁለቱ ሀገራት የፍትሕ ተቋማት መካከል ስለሚኖር ግንኙነት እና ትብብር ውይይት አድርገዋል።