የቀድሞ የፍቅር ጓደኛውን አንገትዋን አንቆ በመያዝ የተለያየ የሰውነት አካሉዋን በቢላ በመውጋት ሕይወትዋ እንዲያልፍ ያደረገው ተከሳሽ በፅኑ እስራት ተቀጣ

Defendant Sentenced to Rigorous Imprisonment for Strangling Former Girlfriend and Stabbing Her to Death

በላይ እርቅይሁን ተፈሪ የተባለ ተከሳሽ በ1/6/2015 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 3፡30 ሲሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ከረሜላ ህንፃ እየተባለ በሚጠራው አከባቢ በፍቅር ጓደኝነት አብራው ስትኖር ቆይታ ባለመስማማታቸው የተለየችውን ሟች ውርጂ አልዩን አብረን እንሁን ብያት ፈቃደኛ አልሆነችም በሚል አንገትዋን አንቆ በመያዝ የተለያየ የሰውነት አካሉዋን በቢላ በመውጋት ሕይወትዋ እንዲያልፍ በማድረጉ ምክንያት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በሴቶችና ህጻናት ላይ ሚፈፀሙ ወንጀሎች ዓ/ሕግ ዳይሬክቶሬት በወ/ሕ/አ 539/1/ሀ መሠረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዓ/ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኃላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ ሁለት የመከላከያ ምስክሮች በማቅረብ ያሰማ ቢሆንም የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በ20/10/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ በ16 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኑዋል፡፡

Tagged Under: 2015 • 2016 • ababa • addis • addis ababa police commission • capital punishment • commission • conviction • court • Criminal Code • district • domestic • Domestic Violence • federal • Federal High Court • femicide • high • imprisonment • lideta • lideta district court • manslaughter • Murder • Police • rigorous • Rigorous Imprisonment • Sentencing • Stabbing • strangulation • violence
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች