ከትዳር አጋሩ ውጪ የፍቅር ጓደኛው የነበረችውን እና እሷን ተከትሎ ከቤት በመውጣት በዱላ ሊመታኝ ነበር ያለውን ግለሰብ የገደለው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ

Defendant Sentenced to Imprisonment for Killing a Man Who Allegedly Exited a House with a Stick to Assault Him Following His Visit to His Extramarital Partner

ጫካ አሰፋ ዳዲ የተባለ ተከሳሽ የካቲት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 4፡30 ሲሆን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አላንጉራ መንደር 3 እየተባለ በሚጠራው ሰፈር ከትዳር አጋሩ ውጪ የፍቅር ጓደኛው የሆነችውን የግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት ሳንኳኳ ከግል ተበዳይ ኋላ ወንድ የግል ተበዳይ ተከትሎ በመምጣት በዱላ ጭንቅላቴን ሊመታኝ ብሏል በሚል ምክንያት ከትዳር አጋሩ ውጪ የፍቅር ጓደኛው የነበረችውን እና እሷን ተከትሎ ከቤት በመውጣት በዱላ ሊመታኝ ብሎ ነበር ያለውን ግለሰብ በሕጋዊ መንገድ ይዞት በነበረው ሽጉጥ ተኩሶ በመግደሉ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶችና ህጻናት ላይ ሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በወ/ሕ/አ 540 መሠረት በእያንዳንዱ የግል ተበዳዮች ሁለት ተደራራቢ ክስ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ የመከላከያ ምስክሮችን በማቅረብ ያሰማ ቢሆንም የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

Tagged Under: ababa • addis • addis ababa • affair • amhara region • assault • case • conviction • court • criminal • Criminal Case • Domestic Violence • extramarital • extramarital affair • federal • Federal High Court • firearm • high • Homicide • imprisonment • Legal Proceedings • lideta • manslaughter • Murder • murder charge • police investigation • Prosecution • self-defense • sentence • testimony
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች