የኢትዮዽያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር በአዋጅ ቁ.1249/2013 ተቋቁሞ የማህበሩን መሪዎች ከሾመ በኋላ የማህበሩ የተለያዩ መዋቅሮች፣ የስራ ክፍሎች እና አሰራሮች ለማደራጀት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል።
የማህበሩን ቅርፅና አደረጃጀት የሚወስነው የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ እና ሌሎች ረቂቃቸው የተጠናቀቀ 5 መመሪያዎች በጠበቆችና ባለድርሻ አካላት ውይይት የተደረገባቸው መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡
ረቂቅ የመተዳደሪያ ደንቡ የጠበቆች ማህበሩ ሀገራችንን ጨምሮ በአፍሪካ፣ በአውሮፖና በአሜሪካ ያሉ በርካታ Bar Associations መዋቅሮችን በማጥናት ተወዳዳሪ መዋቅር እንዲኖረው ለማስቻል የተሞከረበት ነው:: ረቂቁ ሰነዱ በጠቅላላ ጉባኤ እስኪፀድቅ ድረስ እየተመከረበት ይገኛል::
ለዚሁ ስራ የተደራጀውና በማህበሩ መሪዎች አስተባባሪነት የተዋቀረው በዘርፉ የካበተ ልምድ ያላቸው አንጋፋ ጠበቆችን የያዘው ግብረ ኃይል ስራውን ጀምሯል::
የስራ ቡድኑ በአዲስ አበባ ራስ ሆቴል በመገናኘት ውጤታማ ውይይት አድርጓል:: በዚህም ረቂቁን የበለጠ በማዳበር በዚህ የተቋሙን አደረጃጀትና አሠራር በሚወስነው ታሪካዊ ሰነድ ላይ የበኩሉን በጎ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል::