ወንጀልን በመከላከል ተግባር ዉስጥ ማህበረሰብን ማሳተፍ አማራጭ ሳይሆን ግዴታ መሆኑ ተመላከተ

Community Engagement in Crime Prevention is an Obligation Not an Option

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በንቃተ ሕግ፣ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት አሰተባባሪነት ወንጀል መከላከል ላይ መሠረት ያደረጉ ተከታታይ ሥልጠናዎች እየተሰጡ ሲሆን፣ በዛሬዉ እለትም ከአዲስ አበባ ፖሊስ እና ከፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ለተዉጣጡ የማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አመራሮች ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሥልጠና በመስጠት ላይ ነዉ፡፡

በማኅበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት አማካኝነት ወንጀልን መከላከል በሚቻሉባቸዉ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ባደረገዉ በዚሁ ሶስተኛ ዙር ሥልጠና፣ የወንጀል ፍትሕ ፖሊስ፣ የተቀናጀ የወንጀል መከላከል ስትራቴጅ እና መሰል ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ተመስርቶ ሥልጠናዉ እንደሚሰጥ በፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸዉ ወርቁ ገልፀዋል።

አያይዘዉም ወንጀልን መከላከል በዋናነት ማኅበረሰብን መሠረት ማድረግ እንደሚገባዉና ይህንኑ ተግባር ለመፈፀም ያስችል ዘንድም የፍትሕ ሚኒስቴር የማስተባበር ሃላፊነቱን በመወጣት ከአዲስ አበባ ፖሊስና ከፌዴራል ፖሊስ ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችለዉን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሞ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አስታዉሰዉ የዛሬዉ የማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ሥልጠናም የዚሁ አካል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የወንጀል ፍትሕ ስርአቱ መግቢያ በር ፖሊስ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ ወንጀልን ለመከላከል ያስችል ዘንድም መሠረታዊ የሆነዉ ነገር መሰራት ያለበት ፖሊስ ጋር መሆኑን በመጠቆም ህብረተሰቡን አስተባብሮ መሥራት ከተቻለ ወንጀልን መከላከል እንደሚቻልም አመላክተዋል፡፡

የማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዲቪዥን ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታዲዮስ አክሊሉ በበኩላቸዉ ሥልጠናዉ በዋናነት እስከታች ያለዉ አደረጃጀት ተገቢዉን ግንዛቤ ጨብጦ ስራዉን እንዲሰራ አጋዥ መሆኑን በመግለፅ ባለፉት ጊዜያቶችም ጉዳዩ ሰፊ ትኩረት ተሰጥቶት ተመሳሳይ ሥልጠናዎች ሲሰጡ መቆታቸዉን አስታዉሰዉ፣ ሥልጠናዉን ላመቻቸዉ የፍትሕ ሚኒስቴር ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።

ሰልጠናዉ በሁለት ቀን ቆይታዉ በማኅበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት የወንጀል ስጋትንና ወንጀል መከላከል፣ የወንጀል መከላከል ስትራቴጅ ምንነት እንዲሁም ማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ሰብዓዊ መብትን መከበርን መሠረት ያደረገ ለማድረግ በሚያስችሉ ርእሰጉዳዮች ላይ ተመስርቶ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

Tagged Under: ababa addis Addis Ababa Police Awareness Capacity Building civil liberties Collaboration community Community Engagement Community Policing Coordination Crime Crime Prevention Criminal Justice federal Federal police fundamental rights Human Rights integrated integrated crime prevention strategy legal Legal Awareness Memorandum of Understanding Police police leadership Police Training policing prevention Training training workshops
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች