በፌዴራል አስተዳደር ስነ ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱ እንደቀጠለ ነው

Awareness Training on Federal Administrative Procedure Proclamation No. 1183/2012 Continues

በፌዴራል አስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ላይ የግንዛቤ ሥልጠና ጥቅምት 23/2016 ዓ.ም የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አመራሮች ተሰጥቷል ።

ሥልጠናውን የሰጡት በፍትሕ ሚኒስቴር የፌዴራል ህጎች ተፈፃሚነት መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ሀወኒ ታደሰ የፍትሕ ሚኒስቴር አንዱ ተልዕኮ የሚወጡ የፌዴራል ህጎችን አፈፃፀም መከታተል መሆኑን ገልፀው የፌዴራል አስተዳደር ሥነ- ስርዓት አዋጅ ዓላማ የመንግሥት አሠራር ግልጽነት እና ተጠያቂነት የሰፈነበት መሆኑን የሚደነግገውን ህገ-መንግስታዊ መርህ ማስተግበር ነው ብለዋል።

አዋጁ የአስተዳደር ተቋማት በዜጎች መብት ላይ የሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት በሕግ እንዲመራ፣ ከሕግ ውጪ በሆነ ጊዜም ዜጎች መብታቸውን በፍርድ ሂደት የሚያስከብሩበት እና አስተዳደራዊ ፍትሕ የሚያገኙበትን እድል መፍጠር መሆኑንም ዳይሬክተሯ ገልፀዋል።

ሥልጠናው የፌደራል አስተዳደር ሥነ- ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ትርጉም፣ ዓላማ፣ ምን ምን ጉዳዮች እንደያዘ፣ በአዋጁ የተቀመጡ የመመሪያ አወጣጥ ሥነ-ስርዓቶች፣ የአስተዳደር ውሳኔ መርህ እና ሂደቶች እንዲሁም እነዚህን ሂደቶች በአግባቡ አለመተግበር የሚያስከትለው ውጤት በሚሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጓል።

ተሳታፊዎችም በቀረበው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ላይ ያላቸውን ጥያቄ እና አስተያየት አንስተው ውይይት ተደርጎበታል።

Tagged Under: 1183/2012 • Accountability • administrative • administrative justice • Administrative Law • awareness training • citizen • Citizen Rights • due • Due Process • ethiopian law • federal • Federal Administrative Procedure Proclamation • Government • Government Administration • Government Transparency • hawani tadesse • law • Legal Compliance • Legal Training • ministry of transport and logistics • procedure • process • proclamation • proclamation no. 1183/2012 • Public Administration • Rights • Rule of Law • Transparency
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች