በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የህንፃ ዕድሳት እና የግቢ ማስዋብ ስራ ለማሰራት ፍትሕ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ስምምነት አካሒዷል፡፡
የፍትሕ ሚኒስቴርን ወክለው የተገኙት የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽንን ወክለው የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ሽመልስ እሸቱ ስምምነቱን ፈርመዋል፡፡
የሕንፃ ዕድሳቱና ማስዋብ ስራው በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶች ለተገልጋዮች ምቹና በቴክኖሎጂ የታገዙ እንዲሆኑ የሚያስችል እንዲሁም ሰራተኞች በተመቻቸ ሁኔታ ስራቸውን እንዲያከናውኑ የሚያደርግ ሲሆን ስራው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ይጠበቃል፡፡
የአማካሪነት ስራው በቺታ ኮንሰልቲንግ የሚከወን መሆኑ በስምምነቱ ተጠቅሷል፡፡