ሰው የመነገድ፣ ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገርና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ለሥራ ወደ ውጭ ሀገር የመላክ ወንጀል መከላከልና ከምሰክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ ጋር በተያያዘ ውይይት

A Discussion on Human Trafficking, Smuggling, and Protection against Criminal Exploitation

ውይይቱ የተካሄደው በዛሬው ዕለት ሲሆን የፍትሕ ሚኒስቴር፣ የአሜሪካ ኢምባሲና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአደገኛ መድሃኒትና ወንጀል ጉዳይ የምሰራቅ አፍሪካ ፕሮግራም የሰራ ኃላፊዎችና የባለሙያዎች ቡድን ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በውይይት መድረኩም በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ፍቃዱ ፀጋ የወንጀል ፍትሕ አሰተዳደር ተግባር ውጤታማ እንዲሆን ከመሥራት አንፃር በተለይም በሰው የመነገድ፣ ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገርና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ለሥራ ወደ ውጭ ሀገር የመላክ ወንጀልን ከመከላከል እንዲሁም ከምሰክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ ጋር ተያይዞ በአቅም ግንባታ፣ በግብዓትና ስትራቴጅክ ጉዳዮች ዙሪያ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ልቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

ሚኒስትር ዴዔታው ይህንን ያሉት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአደገኛ መድሃኒትና ወንጀል ጉዳይ (UNODC) ጽ/ቤት ድጋፍ በሰው የመነገድ፣ ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገርና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ለሥራ ወደ ውጭ ሀገር የመላክ ወንጀልን ከመከላከል እንዲሁም ከምሰክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ ጋር ተያይዞ በአቅም ግንባታ፣ በግብዓትና ስትራቴጅክ ጉዳዮች ዙሪያ እንደ ሀገር የተሰሩ ስራዎችን ለአሜሪካ ኢምባሲና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአደገኛ መድሃኒትና ወንጀል ጉዳይ የምሰራቅ አፍሪካ ፕሮግራም የሰራ ኃላፊዎች ገለጻ በተደረገበት ወቅት ነው፡፡

በመድረኩም በሰው የመነገድ፣ ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገርና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ለሥራ ወደ ውጭ ሀገር የመላክ ወንጀልን ከመከላከል እንዲሁም ከምሰክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ ጋር ተያይዞ UNODC እያደረገ ያለው እገዛ በዘርፉ ከፍተኛ ዉጤት እያስመዘገበ እንዳለ የተጠቆመ ሲሆን ዓለም ዓቀፍ ትብብርን ከማጠናከር እንዲሁም ውጤታማ የምርመራና ክስ ስራ ከመሥራት አንጻር ያሉ ክፍተቶቸን ለመሙላት የሚደረጉ ጥረቶችን በማገዝ እንዲሁም ከምሰክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ ጋር በተያያዘ ያሉ ዓለም ዓቀፍ ተሞክሮዎችን ከመቅሰምና ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር በስፋት ሊሰራ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

በሕገ-ወጥ መልኩ ለሚካሄደው የሀገር ውስጥ የፍልሰተኞች ዝውውርም ከፍተኛ ትኩረት ስጥቶ መሥራት እንደሚገባና የዘርፉን ስራ ለማገዝ የሚረዱ ቅንጅታዊ አሰራሮችና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማስፋፋት እንደሚገባ የተጠቆመ ሲሆን UNODCም የዘውትር ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቋል፡፡በውይይቱ ከአሜሪካ ኢምባሲና ስቴት ዲፓርትመን የህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መቆጣጠር እና መከላከል ጉዳዮች ኮኖር ማክጊየር፣ ኬሪ ማክብሪድ፣ ጀስቲን ፖላርድና ትዝታ አዱኛ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት አደገኛ መድሃኒትና ወንጀል ጉዳይ ደግሞ በምስራቅ አፍሪካ ድንበር ተሻጋሪና የተደራጁ ወንጀሎች፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና የሽብር መከላከል ፕሮግራም ኃላፊ ማሪያ ተመስቫሪ፣ የወንጀል መከላከል እና የወንጀል ፍትሕ ኦፊሰር ጁሊየስ ለማኮ እንዲሁም የብሔራዊ ፕሮግራም ኦፊሰር ሌሊሰ ተርፋሳ ተሳታሲ የሆኑ ሲሆን በተደረገላቸው ገለጻ ደስተኛ መሆናቸውንና ኢትዮጵያ በዘርፉ ከጊዜ ወደጊዜ እያሰመዘገበች ያለው ውጤት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ ከዘርፉ ጋር በተያያዘ አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ትብብርና ድጋፍ አንዲሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

Tagged Under: building • capacity • Capacity Building • counter-trafficking • Crime • criminal • Criminal Investigation • criminal justice reform • cross-border • Cross-Border Crime • East Africa • human • Human Trafficking • informant • Informant Protection • International Cooperation • Law Enforcement • organized • Organized Crime • Police • protection • Security • Smuggling • strategic partnerships • trafficking • Transnational crime • UNODC • witness • Witness Protection
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች