መሰረተ ማኅበረሰብ ፍትሕ

ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎች በተለያዩ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ባህላዊ እና ኃይማኖታዊ መዋቅር ውስጥ የቆዩ የማኅበረሰብ ፍትሕ አገልግሎት መስጫ ዘዴዎች ናቸው። እንደ ሽምግሊና/ጃርሱማ፣ አፎቻ፣ ገረበ፣ ጉዱማሌ እና ሃይማኖታዊ ሽምግልና ያሉ ግጭቶችን ለመፍታት፣ ሰላም ለማስፈን እና እርቅን ለማስፋፋት ጥቅም ላይ የሚውሉ ዘዴዎች ናቸው። እነዚህ ተቋማት የማኅበረሰብ ፍትሕ አገልግሎት መስጫ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ዘመናዊ  ፍርድ ቤቶች ከመጀራቸው በፊት ነበር።

ነገር ግን፣ ዘመናዊ ፍርድ ቤቶች በአገራችን ከተጀመሩ በኋላ የነበረው የጠበበ ዘመናዊ አመለካከት መደበኛው ፍትሕ ሥርዓት እነዚህን አገር በቀል ተቋማት እንደ ደጋፊ ሳይሆን እነደ ኋላቀር አድርጎ በመመልከት ችላ ብሎዋቸው ቆይቷል ። 

በኢትዮጵያ በ HiiL የተደረገው የJustice Needs Assessment ጥናት ውጤት እንደሚያሳየው፡-

  • ከ43% በላይ የሚሆኑት አለመግባባቶች የሚፈቱት ከመደበኛ ፍርድ ቤቶች ይልቅ በልማዳዊ ወይም መደበኛ ባልሆኑ መንገዶች ነው፣
  • እነዚህ ዘዴዎች ተደራሽ፣ የአገልግሎት ዋጋቸው ተመጣጣኝ በመሆኑ እና እርቀ-ሰላም ላይ የሚያተኩሩ በመሆናቸው ማኅበረሰቡ ከፍ ያለ ቦታ ይሰጣቸዋል፣
  • ማኅበረሰቡ በሽማግሌዎች እና ኃይማኖት መሪዎች ላይ ያለው አመኔታ ከፍ ያለ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህ ሥርዓት ሕገመንግሥት እና ሰብዓዊ መብቶች ጋር በተጣጣመ መልኩ እንዲተገበር ይፈልጋል።
0 % በላይ

የሚሆኑት አለመግባባቶች የሚፈቱት ከመደበኛ ፍርድ ቤቶች ይልቅ በልማዳዊ ወይም መደበኛ ባልሆኑ መንገዶች ነው።

በመሆኑም የባህላዊ እና መደበኛ ፍትሕ ሥርዓትን ለማስተሳሰር የባህላዊ ፍርድ ቤቶች እና ሌሎች የማኅበረሰብ ፍትሕ አገልግሎት ዘዴዎች ተደራሽነታቸውን እና ሕጋዊነታቸውን ጠብቀው በሰብዓዊ መብት ማዕቀፍ ውስጥ እንዲሰሩ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎች በተለይም በገጠር አካባቢዎች በስፋት ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ እና በማኅበረሰቡ እምነትም የሚጣልባቸው ሲሆን የተለያዩ ክልሎች ለባህላዊ ፍርድ ቤቶች እውቅና በመስጠት አገልግሎቱ እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በ2013 ለባህላዊ ፍርድ ቤቶች እውቅና ከሰጠ በኋላ 1,133,374 ጉዳዮች በባህል ፍርድ ቤቶች ቀርበዉ እልባት አግኝተዋል። የሲዳማ፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ደቡብ ምዕራብ እትዮጵያ ክልሎች በክልላቸው ምክርቤት ሕግ በማውጣት ለባህላዊ ግጭት አፈታት እውቅና የሰጡ ክልሎች ናቸው።

በሌላ በኩል ፍትሕ ሚኒስቴር እነደ HiiL (The Hague Institute for Innovation of Law) ካሉ ዓለም ዓቀፍ አጋሮች ጋር በመሆን ማኅበረሰብ ዓቀፍ የፍትሕ አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን እየደገፈ ይገኛል። በዚህ መሰረት በሲዳማ፣ በአፋር እና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማዕከላትን በመክፈት አገልግሎት እንዲሰጡ በመደረግ ላይ ይገኛል።

ክልሎች በማኅበረሰብ ፍትሕ ላይ ያላቸውን ሁኔታ ይመልከቱ

Tigray
Afar
Amhara
Oromia
Somali
BG
Gambella
Harari
Sidama
SWE
South Eth.
CE
Diredawa
Addis Ababa

Community Justice

The Ministry of Justice, together with international partners like HiiL (The Hague Institute for Innovation of Law), is supporting people-centered justice programs to connect community mechanisms with formal institutions. Community center justice inaugurated and operationalized in Sidama, Afar and Addis Ababa City Administration. The Ministry of Justice, together with international partners like HiiL (The Hague Institute for Innovation of Law), is supporting people-centered justice programs to connect community mechanisms with formal institutions. Community center justice inaugurated and operationalized in Sidama, Afar and Addis Ababa City Administration.