የፍትሕ ሚኒስቴር የህብረተሰቡን ንቃተ ህግ ለማሳደግ የዳሰሳ ጥናት እያካሄደ ነው

ፍትሕ ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር 943/2008 (በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 40 እንደተሻሻለው) በተሰጠው ሥልጣን እና ኃላፊነት መሠረት ከሚያከናውናቸው ስራዎች መካከል የህብረተሰቡን ንቃተ ሕግ ማሳደግ አንዱ ነው፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ይህንኑ ስራ በ2017 በጀት ዓመት ጥናት እና ፍላጎት ላይ በማተኮር ስራውን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

በ2018 የበጀት አምትም ውጤታማ የንቃተ ሕግ ስራ ለመሥራት እንዲያስችል ማህበረሰቡ ንቃተ ሕግ የሚፈልግባቸውን የሕግ ርእሰ ጉዳዮች ለመለየት የዳሰሳ ጥናት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ እርሶም ይሄንኑ በመረዳት ከዚህ በታች በተዘጋጀው የጎግል ፎርም ላይ ለተዘጋጁ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ለጥናቱ አጋዥ ሚናዎን እንዲወጡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

https://docs.google.com/…/1FAIpQLSdUrEwamp0O63…/viewform

በየንቃተ ሕግ፣ ትምህርና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

ይህንን ጋዜጣዊ መግለጫ ያጋሩ

ፌስቡክ
ኤክስ
ሊንክዲን
ቴሌግራም

ሌሎች ጋዜጣዊ መግለጫዎች