
መሪማ መካ አዴላ ፍትህ ሚኒስቴርን ከተቀላቀለችበት 2007 ዓም ጀምሮ በዐ/ህግነት የስራ መደብ ላይ በህግ እና በተቋሙ የተጣለባትን ሀላፊነት ስትወጣ የቆየች ሲሆን በተለይም በቡድን መሪነት በተለያዩ የስራ ክፍሎች ስታገለግል ከቆየች በኋላ በተለያዩ የተቋሙ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ላይ በምክትል ሀላፊነት ስታገለግል ቆይታ በ2016 ዓም ጀምሮ በሀላፊነት የስራ መደብ ላይ ያለችና በተለይም በአዲስ መልክ ተቋቁሞ ወደ ስራ የገባውን ለሚኩራ ቅ/ጽ/ቤት ከሌሎች የሥራ ባልደረቦች ጋር በጋራ በመሆን በአግባቡ ተደራጅቶ ስራዎች እንዲጀመሩ የበኩሏን ሀላፊነት በመወጣት በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ እያገለገለች ትገኛለች፡፡