
ማስተዋል አዳነ አሰፋ ፍትህ ሚኒስቴርን ከተቀላቀለችበት 2009 ዓም ጀምሮ በዐ/ህግነት የስራ መደብ ላይ በህግ እና በተቋሙ የተጣለባትን ሀላፊነት ስትወጣ የቆየች ሲሆን በተለይም በቡድን መሪነት ስታገለግል ከቆየች በኋላ በአራዳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶት በምክትል ሀላፊነት አገልግላለች በ2017 ዓም ጀምሮ በሀላፊነት የስራ መደብ ላይ ያለችና በተለይም በእርሷ አመራር የስራ ክፍሉ በተሳካ ሁኔታ በማስተባበር ክህሎት፣ በየትኛውም ደረጃ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር አብሮ በመስራት ፍትሕን ለማስፈን እና እኩልነትን ለማረጋገጥ የበኩሏን ሀላፊነት በመወጣት በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ እያገለገለች ትገኛለች፡፡