ልደት ሙሉጌታ ሊበን

የጉለሌ ቅርንጫፍ ቢሮ ሀላፊ
ግንቦት 6፣ 2005 ዓ.ም. – አሁን

ልደት ሙሉጌታ ከጥር 06 2005 ዓ.ም እስከ የካቲት 24 2014 ዓ.ም ድረስ በቂርቆስ ቅ/ፅቤት በዐ/ህግነት እንዲሁም ከ2014 እስከ ታህሳስ 28/2016 ዓ.ም ድረስ በፍትህ ሚኒስቴር ቂርቆስ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ እንዲሁም ከታህሳስ 29 2016 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በሀላፊነት በጉለሌ ቅ/ጥ/ቤት ሃላፊ በመሆን በስራ ላይ ትገኛች።

ልደት ሙሉጌታ የስራ ቦታዎች ለሰራተኞች እና ለተገልጋዮች ምቹ በማድረግ ፤ሰራተኞችን አስተባብሮ በመምራት፡በማሰራት እንዲሁም በየትኛውም ደረጃ ከሚገኙ ባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር አብሮ በመስራት መልካም ግንኙነት በመፍጠር ቀልጣፋ፣ፍትሃዊና ውጤታማ የፍትህ አገልግሎት መስጠት አስችላለች፡፡

አሁን ካለችበት የአመራርነት ተልዕኮ አስቀድሞ በዐቃቢ ህግነት ከምርመራ እስከ ችሎት ክርክር በመሳተፍ፣ በቡድን መሪነት እንዲሁም በሃላፊነት በአጠቃላይ ከ12 ዓመት በላይ በመስራት በርካታ ልምዶችንና ክህሎት ያካበተችና እነዚህን ልምዶችና ክህሎት በመጠቀም ለወደፊት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ፍትህን ለማስፈን እና እኩልነትን ለማረጋገጥ የህግ ማከብርና ማስከበር ኃላፊነቱን ለመወጣት ዝግጁና ብቁ ናት።

የትምህርት ዳራ

ጅማ ዩንቨርስቲ የህግ ዲግሪ