
ፍፁም መብራቱ ከየካቲት 2013 ዓ.ም ጀምሮ በፍትህ ሚኒስቴር የካ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በም/ሀላፊነት እንዲሁም ከጥቅምት 2015ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በሀላፊነት በመምራት ላይ ይገኛል። በእርሱ አመራር የስራ ክፍሉን መምራት ከጀመረ ወዲህ የስራ ክፍሉ በግቦቹ ላይ ስኬታማ ውጤት ማስመዝገብ በመቻሉ በ2014ዓ.ም በጀት ዓመት በስራ አፈፃፀም 3ኛ ደረጃ እንዲሁም በ2015ዓ.ም በጀት ዓመት 1ኛ ደረጃ አፈፃፀም በማምጣት ቅ/ፅ/ቤቱ በተቋሙ እንዲሸለም አስችሏል፡፡
ፍፁም የስራ ቦታዎች ለሰራተኞች እና ለተገልጋዮች ምቹ በማድረግ ፤ሰራተኞችን አስተባብሮ በመምራት፡በማሰራት እንዲሁም በየትኛውም ደረጃ ከሚገኙ ባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር አብሮ በመስራት መልካም ግንኙነት በመፍጠር ቀልጣፋ፣ፍትሃዊና ውጤታማ የፍትህ አገልግሎት መስጠት አስችሏል፡፡
አሁን ካለበት የአመራርነት ተልዕኮ አስቀድሞ በዐቃቢ ህግነት ከምርመራ እስከ ችሎት ክርክር በመሳተፍ፣ በቡድን መሪነት እንዲሁም በምክትል ሀላፊነት በአጠቃላይ ከ15 ዓመት በላይ በመስራት በርካታ ልምዶችንና ክህሎት ያካበተና እነዚህን ልምዶችና ክህሎት በመጠቀም ለወደፊት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ፍትህን ለማስፈን እና እኩልነትን ለማረጋገጥ የህግ ማከብርና ማስከበር ኃላፊነቱን ለመወጣት ዝግጁና ብቁ ነው።
ሀረማያ ዩኒቨርስቲ፣ የህግ ዲግሪ