
ኤባ አበበ ከሚያዝያ 2016 ዓ.ም ጀምሮ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆኖ እየሰራ ይገኛል። ኤባ የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ እና ህዝቡ በፍትህ ስርዓቱ ላይ ያለውን እምነት በማሳደግ ረገድ ትልቅ ሚና የተጫወተ ጠንካራ የህግ ባለሙያ እና ኃላፊ ነው። አሁን ወዳለበት የአመራር ቦታ ከመምጣታቸው በፊት በዐቃቤ ሕግ፣ በወንጀል ምርመራና ፍትሐዊ ዉሳኔ የማሰጠት የስራ ሂደት ባለቤት፣ በጽ/ቤት ኃላፊነት፣ በ አስተባባሪነትና በሕግ አሰልጣኝነት ከወረዳ እስከ ፌዴራል ከፍተኛ ልምድ ያለው አመራር እና ባለሙያ በመሆን ሰርተዋል። በአገር አቀፍ ደረጃ ከባድ እና ወስብስብ የሆኑ ወንጀሎች እንደ የተደራጁ እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን እና የሙስና ወንጀሎችን በመመርመር፣ በመክሰስ እና ተከራክሮ ዉሳኔ በማሰጠት ከፍተኛ ልምድ ያለው ባለሙያ ነው። በአጠቃላይ ኤባ ከ16 ዓመታት በላይ ባአካበተዉ የህግ ሙያዊ ልምድ በፍትህ ዘርፉ በኃላፊነት እና በታማኝነት ለመስራት ከፍተኛ ብቃት እና ዝግጁነት ያለው ነው።