አሰፋ ማሬ

የልደታ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ
ሚያዚያ 1፣ 2009 ዓ.ም. – አሁን

አሰፋ ማሬ ከነሀሴ 2015ዓ/ም ጀምሮ በፍትህ ሚኒስቴር የልደታ ቅ/ፅ/ቤት የስራ ክፍልን በመምራት ላይ ይገኛል። በእርሱ አመራር የስራ ክፍሉን መምራት ከጀመረ ወዲህ የስራ ክፍሉ በግቦቹ ላይ ስኬታማ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል፡፡አሰፋ የስራ ቦታዎች ለሰራተኞች እና ለተገልጋዮች ምቹ በማድረግ ፤ሰራተኞችን አስተባብሮ በማሰራት እንዲሁም በየትኛውም ደረጃ ከሚገኙ ባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር አብሮ በመስራት መልካም ግንኙነት በመፍጠር ቀልጣፋ፣ፍትሃዊና ውጤታማ የፍትህ አገልግሎት መስጠት አስችሏል፡፡አሁን ካለበት የአመራርነት ተልዕኮ አስቀድሞ በዐቃቢ ህግነት ከምርመራ እስከ ክርክር በመሳተፍ፣ በቡድን አስተባባሪነት እንዲሁም በምክትል ሃላፊነት ከ10 ዓመት በላይ በመስራት በርካታ ልምዶችንና ክህሎት ያካበተና እነዚህን ልምዶችና ክህሎት በመጠቀም ለወደፊት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ፍትሕን ለማስፈን እና እኩልነትን ለማረጋገጥ የህግ ማከብርና ማስከበር ኃላፊነቱን ለመወጣት ዝግጁ ነው።

የትምህርት ዳራ

  • ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ በህግ  የመጀመሪያዲግሪ
  • በህግ ሁለተኛ ዲግሪ ከኢትዬጲያ ሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርሲቲ