አባተ ታደሰ

የአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ
ጥቅምት 30፣ 1993 ዓ.ም. – አሁን

አባተ ታደሰ፣ ከሚያዚያ 2016 ዓ/ም ጀምሮ የአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትን በኃላፍነት እየመራ ይገኛል፡፡

በእርሱ አመራር ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በተሳካ ሁኔታ የወንጀል ሕግን በማስከበር፣ የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ፣ የመንግሥትንና የሕዝብን መብትና ጥቅሞች በተሟላ ሁኔታ የሚያስጠብቅ ጠንካራ የሕግ አስከባሪ የዓቃቤ ሕግ ተቋም ይሆን ዘንድ የበኩለን የኃላፊነት ሚና ባግባቡ ተወጥቷል፡፡

አባተ፣ በማስተባበር ክህሎቱ፣ በየትኛውም ደረጃ ከሚገኙ ከውስጥና ከውጭ ባሇድርሻ እና አጋር አካላት ጋር አብሮ በመስራት፣ በአሳታፊነትና ተጠያቂነት የሚሠራ፣ ውጤታማና ቀልጣፋ የወንጀል ፍትህ አገልግሎት አሰጣጥን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ስኬታማ ነው፡፡

አሁን ካሇበት የአመራርነት ተልዕኮ አስቀድሞም፣ ከጠቅላላው የአገልግሎት ዘመኑ ውሰጥ፣ ወደ ግማሽ የሚጠጋውን ጊዜ፣ ከዞን ፍትህ ጽ/ቤቶች ኃላፊነት አንስቶ፣ በክልልና በፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ፣ በተሇያዩ ማስተባበሪያዎችና ዳይሬክቶሬቶች ደረጃ፣ በአስተባባሪነትና በኃላፊነት ሲያገሇግል የቆየ ሲሆን፣ በዋናነት የሕዝብ አመኔታ ያሇው፣ ውጤታማና ቀልጣፋ የወንጀል ፍትህ አስተዳደር እውን እንዲሆን በማድረግና የመንግሥትንና የሕዝብን መብትና ጥቅሞች በተሟላ ሁኔታ በማስጠብቅ ላይ አተኩሮ ሰርቷል። ከ23 ዓመታት በላይ ያካበተውን የስራ ልምድ በመጠቀም፣ ውጤታማና ቀልጣፋ የወንጀል ፍትህ አስተዳደርን በማስፈንና የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ፣ የመንግሥትንና የሕዝብን መብትና ጥቅሞች
በተሟላ ሁኔታ የማስጠብቅ ኃላፊነቱን በሚገባ ሇመወጣት ብቁና ዝግጁ ነው።

የትምህርት ዳራ

ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ፣ የህግ ዲግሪ