ቀን: ሰኔ 2016 ዓ.ም.
የገቢዎች ሚኒስቴር
Ministry of Revenues

የገቢዎች ሚኒስቴር የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 አፈፃፀም የዳግም ክትትል ሪፖርት

የዚህ ክትትሌ ዓላማ በገቢዎች ሚኒስቴር የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ አፈጻጸም ላይ የመጀመሪያው ዙር ክትትሌ ከተደረገ በኋላ የአዋጁን አፈጻጸም ለማሻሻል የተሰጡ ምክረ-ሀሳቦችን ተግባራዊ ከማድረግና የመሻሻያ እርምጃ ከመውሰድ አንጻር ያለበትን ደረጃ ለመገምገም ይህ ዲግም ክትትሌ ተደርጓል።

የመረጃ ምንጭን በተመለከተ የመጀመሪያውን ዙር ክትትሌ ሪፖርት እንደ መነሻ በመውሰድ ቃለ-መጠይቅ፣ የሕጎች ዲሰሳ እና የአቤቱታ ማቅረቢያ ቅጾች እና የአስተዳደራዊ ውሳኔ የሰነድ ማስረጃዎች ናቸው። ከመረጃ አሰባሰብ ጋር በተያያዘ ዓላማ መር (purposive sampling technique) የናሙና አወሳሰድ ዘዴን በመጠቀም ከመመሪያ ማውጣትና አስተዳደራዊ ውሳኔ መስጠት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸውን የተመረጡ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ቃለ-መጠይቅ ተደርጓል። እንዲሁም የቡድን ውይይት ተደርጓል። አስተዳደር ውሳኔ ናሙናዎችን ከየውሳኔዎቹ አይነት በዘፈቀደ በመምረጥ ለማየት ተችሏል።

የመመሪያ አወጣጥ ሂደትን ከመከተል አንጻር በተወሰኑ መመሪያዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የማድረግ እና መመሪያን ለፍትህ ሚኒስቴር ከማስመዝገብ አንጻር በከፊል የተከናወኑ ተግባራት መሆናቸው ታይቷል። ይህም ከተሻሻለት አምስት መመሪያዎች ውስጥ በሶስቱ ላይ የማብራሪያ ጽሁፍ የተዘጋጀ መሆኑ፣ ከባለድርሻ አካላት በተወሰኑት መመሪያዎች ላይ የውይይት መድረክ መዘጋጀቱ እና ሶስት መመሪያዎች ለመዝገባ ለፍትህ ሚኒስቴር የተላኩና የተመዘገቡ መሆኑ ማሳያዎች ናቸው።

ይሁን እንጂ በተለይ መዝገብ ማድረግ፣ ማስታወቂያ በጋዜጣ ወይም በድረ-ገጽ ማውጣት፣ የውይይት መድረክ ማዘጋጀት፣ ለባለድርሻ አካላት ረቂቁን ለአስተያየት መላክና የጽሁፍ አስተያየት መቀበል እና የመመሪያዎችን ቅጂ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ከማዘጋጀት አንጻር አሁንም ያለቀረፈ ችግር መሆኑ ታይቷል።

በአዋጁ የተመለከቱትን የአስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ መርሆዎችን ከመከተል አንጻር የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 ተመሳሳይ መርሆዎችን የያዘ በመሆኑ በዚህ ረገድ የገቢዎች ሚኒስቴር አፈጻጸም እምብዛም ችግር አይታይበትም።

ከመመሪያ አወጣጥ ሂደት ጋር በተያያዘ የታየውን ሰፊ ክፍተት ልዩ ትኩረት በመስጠት መቅረፍ እንዲገባ በደጋሚ ምክረ-ሀሳብ ቀርቧል።

ሪፖርቱን ያውርዱ

ተጨማሪ ሪፖርቶች