የንግድ ሥራ አገሪቱ በምትከተለው የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ፖሊሲ መሠረት ተገቢውን አሠራር ተከትሎ መካሄድ ስላለበት፤
ኢኮኖሚያዊ ቀልጣፋነትንና ማኅበራዊ ደኅንነትን ለማስፈን እና በነጋዴዎችም መካከል የሚደረጉትን ፀረ-ውድድር የሆኑ ተግባራት በመቆጣጠር ለውድድር አመቺነት ያለው ሥርዓት ማሳደግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
መሠረታዊ በሆኑ አንዳንድ የንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላይ እጥረት በሚያጋጥምበት ወቅት በተጠቃሚው ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ዋጋን መቆጣጠርና ሥርጭቱንም ሥርዓት ማስያዙ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•