የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በኳታር መንግስት መካከል የአጠቃላይ ትምህርት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የሳይንሳዊ ምርምር ዘርፍ የመግባቢያ ሰነድ መጋቢት 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 29 ቀን 2011 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፣
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡-