የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሆልዲንግስ ሪፐብሊክ የፌደራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1ሺ263/2ሺ14 የተቋቋመ በመሆኑ፤
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አደረጃጀትና ተግባር የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ መሠረት እንደሚወሰን በአዋጁ የተደነገገ በመሆኑ አደረጃጀቱንና ተግባራቱን ለመደንገግ ደንብ ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ፤
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ስትራቴጂካዊ ፍላጎቶች ለማሟላት በሚያግዝ አኳኋን የግል ኢንቨስትመንት ከመንግስት ጋር በጋራ ልማት ስራዎች ተሳታፊ እንዲሆን የሚያስችል ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የግል ኢንቨስትመንትን በተጠናከረ ሁኔታ ለመሳብ የሚያስችል ተቋማዊ አደረጃጀት መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የተቀናጀ ስትራቴጂያዊ ቁጥጥር በማከናወን በመንግስት ባለቤትነት የተያዙ ሪል-ስቴት፣ መሬት፣ መሠረተ-ልማቶች፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች እና የመሳሰሉት ሀብቶችን የተሟላና ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዲሰጡ ማድረግ የሚቻልበትን ተቋማዊ አደረጃጀት መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የመንግስት የሆኑ ሀብቶችን እና የሀብት ምንጮችን በማስተዳደር ረገድ ተገቢውን የገበያ ሥርዓትን በመከተል፣ በጠንካራ የኩባንያ መልካም አስተዳደር መርሆዎች የሚመሩ እንዲሆኑ ለማስቻል፤
ባለቤትነታቸው የፌደራል መንግስት የሆኑ የተለያዩ ሃብቶችን በአንድ ሕጋዊ ተቋም ስር እንዲተዳደሩ በማድረግ መንግስት ተገቢውን እና ዉጤታማ አመራር እንዲሰጥ ማስቻል እንዲሁም ከፍ ያለ የውጪ ኢንቨስትመንት እና ቴክኖሎጂ መሳብ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1ሺ263/2ሺ14 አንቀጽ 103 መሠረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚከተለውን ደንብ አውጥቷል።
•
•
•
•