በአገልግሎት ላይ

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና አዋጅ

በኢኮኖሚ ረገድ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመዝለቅ ክህሎት ያለው፣ በዲሲፕሊን የታነፀ፣ ተነሳሽነት የተላበሰና ከአዳዲስ አሠራሮች ጋር ተዋህዶ ሥራውን የሚያከናውን የሰው ኃይል ማፍራት ያለውን ወሳኝ ድርሻ በመገንዘብ፤

በገበያ ፍላጐት የሚመራ አስፈላጊ የሰው ኃይል ማፍራት የሚቻለው በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሥርዓት በኩል መሆኑ በመታመኑና የሃገራችን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ስትራቴጂም የሰው ኃይል ግንባታው በዚሁ አቅጣጫ እንዲመራ የተወሰነ በመሆኑ፤

በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ አገር አቀፍ የሙያ ደረጃ በማዘጋጀትና የሙያ ብቃት ምዘና ሥርዓት በማደራጀት በተለያዩ መንገዶች ክህሎት የጨበጡ የማህበረሰብ አባላት ወጥ በሆነ የምዘና ሥርዓት ተመዝነው አገር አቀፍ እውቅና ያለው ማረጋገጫ የሚያገኙበትና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚሆን የሰው ኃይል ማፍራት እንደሚገባ በመታመኑ፤

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሥርዓቱ በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በገበያ ተወዳዳሪነት የማረጋገጥ ሚና እንዲጫወት ማድረግ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፤ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሥርዓቱ ወጥነት ይኖረው ዘንድ በአንድ በኩል አገር አቀፍ የአስተዳደር ማዕቀፍ በመደንገግ በሌላ በኩል ደግሞ ያልተማከለና አሳታፊ የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት በማመቻቸት ባለድርሻ አካላት በንቃት የሚሳተፉበት አሠራር መፍጠር በማስፈለጉ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡-

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 954/2008
ቀን: ግንቦት 19፥ 2008 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

No data was found