ቀደም ሲል በአዋጅና በተለያዩ ደንቦች ወደ ውጭ አገር በሚላክ ቡና ላይ ተጥለው የነበሩትን የተለያዩ የታክስና የቀረጥ ዓይነቶች ማሰባሰብና አንድ ወጥ ማድረግ ለአፈጻጸም አመቺ መሆኑ ስለታመነበት በቁርጥ ተጥለው የነበሩትን ቀረጦች ወደ ዋጋ መቶኛ መለወጥ የታክሱን ፍትሐዊነት የሚጠብቅ ስለሆነ፤
በዋጋ መለዋወጥ ምክንያት በገቢ ላይ የሚደርሰውን መዋዠቅ ለመከላከል ገበያውን ተከትሎ የመጣኔ ማስተካከያ ማድረግ የሚቻልበትን አሠራር መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•