በአገልግሎት ላይ

የተፋሰስ ምክር ቤቶችና ባለሥልጣናት አዋጅ

የኢትዮጵያ የውሃ ሀብት ሥርጭቱ በቦታና በወቅት የተዛባ ከመሆኑም በላይ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ባደገ መጠን የውሃ አጠቃቀም ፍላጎት በመጠንም ሆነ በጥራት እንዲጨምር የማድረግ ውጤት የሚያስከትል በመሆኑ፤

የኢትዮጵያ የውሃ ሀብት አስተዳደር ፖሊሲ፣ የፖሊሲው ምሰሶ የሆነውን የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር መርህን ተግባራዊ ለማድረግ የተፋሰስ ምክር ቤቶችና ባለሥልጣናት ማቋቋምን እንአንዱና ዋነኛ መሣሪያ አድርጎ የተቀበለው በመሆኑ፤

የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር፣ ውሃ እንደ ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ሀብትነቱ ልማቱ ሚዛናዊና ቀጣይነት ያለው እንዲሆን በተፋሰስ ውስጥ ያሉ አጠቃቀሞች በአጠቃላይ የሚጣጣሙበትን ሥርዓት መዘርጋትን የሚጠይቅ በመሆኑ፤

የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር፣ በተፋሰስ ውስጥ የሚገኙ አግባብ ያላቸው አካላት ውሳኔዎቻቸው፣ ዕቅዶቻቸውና ተግባሮቻቸው በውሃው ዑደትና በሌሎች ተጠቃሚዎች ላይ በሚያስከትሏቸው ውጤቶች ላይ የአመለካከት፣ የፍላጎትና የግንዛቤ ልዩነት ቢኖራቸውም ተባብረው እንዲሠሩ የሚጠይቅ በመሆኑ፤

የተፋሰስ ምክር ቤቶችና ባለሥልጣናት መቋቋም የተፋሰስ የውሃ ሀብት ዕቅድን መሠረት በማድረግና አግባብነት ባላቸው አካላት ዘንድ ውጤታማና ቀጣይነት ያለው የጋራ አመራር በማስፈን የኢትዮጵያ የውሃ ሀብት አስተዳደር ፖሊሲን በመተግበር ረገድ ብቃት ያለው የተረጋጋ አሠራር እንዲኖር ለማስቻል ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያለው በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 534/1999
ቀን: ሐምሌ 16፥ 1999 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች