በአገልግሎት ላይ

በሰው የመነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ

በሰው የመነገድ፣ ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር እና በህገ-ወጥ መንገድ ለስራ ወደ ውጭ አገር መላክ ወንጀሎች በዜጎች አካል፣ ህይወት እና ደህንነተ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አያደረሱ እና ለሰብዓዊ መብት ጥሰት አያጋለጡ የሚገኙ ወንጀሎች መሆናቸውን በመገንዘብ፤

በሰው የመነገድ እና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር – 909/2007 ግልፅነት የሚጎድለው፣ ከሌሎች ህጎች ጋር የማይጣጣምና ለችግሩ በቂ ምላሽ የማይሰጥ ሆኖ በመገኘቱ በአዲስና በተሟላ የሕግ ማዕቀፍ መተካት በማስፈለጉ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህጉመንግስት አንቀጽ 18 መሰረት በማንኛውም መንገድ በሰው መነገድ በመከልከሉ እንዲሁም በሰው የመነገድ በተለይም በሴቶችና ሕጻናት መነገድን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና ወንጀል ፈፃሚዎችን ለመቅጣት እና ሰውን በሕጉወጥ መንገድ በየብስ፣ በባህርና በአየር ማስወጣትና ማስገባት ለመከላከል የሚያስችሉ ፕሮቶኮሎችን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በማውጣቱና ኢትዮጵያም ስምምነቱን ያፀደቀች በመሆኑ የማስፈጸሚያ ዝርዝር ህግ ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ፤

መንግስት ሰዎች በተፈጥሮ እና በህግ የተጎናጸፉትን መብትና ጥቅም የማክበር እና የማስከበር ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ በወንጀል መከሳከል፡ ወንጀል ፈፃሚዎችን በህግ ተጠያቂ ማድረግ: የተጎጂዎች ጥበቃና መልሶ ማቋቋም በተለይም ለወንጀሉቹ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰቡ ክፍሎችን ተደራሽ የሚያደርግና የተጎጂዎችን ዕድሜ፡ ጸታና ልዩ ፍላጎት ያማከለ ተግባር መፈፀም እና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ማውጣት እና ሥርዓት መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 55 (5) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡”

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 1178/2012
ቀን: መጋቢት 23፥ 2012 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 909/2007

•

ነሐሴ 11፥ 2007 ዓ.ም.
የተሻረ