በጥራትና በዋጋ ተወዳዳሪ የሆኑ የቁም እንስሳት ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማቅረብ የሚያስችል ዘመናዊ የቁም እንስሳት ግብይት ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የቁም እንስሳት ግብይት በወቅታዊ መረጃ የተደገፈ፣ ቀልጣፋ እና ወጪ ቆጣቢ በማድረግ አርቢው፣ ነጋዴው፣ ሸማቹ እና አገሪቱ ከግብይቱ ተገቢውን ጥቅም የሚያገኙበትን ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•