በአገልግሎት ላይ

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ

አሠሪና ሠራተኛ የጋራ ራዕይ ኖሯቸው የሥራ ግንኙነቶቻቸውን መሠረታዊ በሆኑና በህግ በተደነገጉ መብቶችና ግዴታዎች ላይ በመመስረት አስተማማኝ የኢንዱስትሪ ሰላም፤ የዘላቂ ምርታማነት እና የገበያ ተወዳዳሪነት አቅም በመፍጠር ሀገራችን ለተያያዘችው ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት የማስመዝገብ ብሔራዊ ግብ በትብብርና በጋራ እንዲሰሩ ማድረግ ጠቃሚ በመሆኑ፤

ሠራተኞች እና አሠሪዎች የየራሳቸውን ማኅበራት በሙሉ ፈቃድና ነፃነት በማቋቋም በመረጧቸው ህጋዊ ወኪሎች አማካኝነት መብትና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅና ግዴታዎቻቸውን በአግባቡ ለመወጣት የኅብረት ድርድር እንዲያደርጉ፤ በመካከላቸው የሚነሱ የሥራ ክርክሮችም የማኅበራዊ ምክክር ሥርዓትን ጨምሮ በሌሎች አማራጭ መድረኮች በተቀላጠፈ ሁኔታ መፍትሔ እንዲያገኙ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤

መሠረታዊ የሥራ ላይ መብቶችንና ግዴታዎችን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ለኢንቨስትመንትና ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ግቦች መሳካት ምቹ ሁኔታን መፍጠር የሚያስችል የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አስተዳደር ሥርዓት መመስረት እንዲቻል፤ እንዲሁም የሥራ ሁኔታን፤ የሙያ ደህንነት፤ ጤንነትና የሥራ አካባቢ ጥበቃንና የሁለትዮሽ እና የሦስትዮሽ ማኅበራዊ ምክክር አሠራርን በማጠናከር በሕግ መሠረት የማማከርና የመቆጣጠር ተግባራትን እያመጣጠነ ሥራውን የሚያከናውን አካል ስልጣንና ተግባር መዘርዘርና መወሰን በማስፈለጉ፤

እነዚህን ከላይ የተመለከቱትን ዓላማዎች በትክክል መተግበር ይቻል ዘንድ የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነቶች የሚመሩባቸውን መሠረታዊ ሃሣቦች እና የሥራ ሁኔታዎችን የያዘ፤ ከመንግሥት አጠቃላይ የፖለቲካ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ፖሊሲ ጋር የተገናዘበ፤ ኢትዮጵያ ከፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽኖችና ሌሎች ሕጋዊ ሠነዶች ጋር የተጣጣመ ሕግ ለማውጣት በሥራ ላይ ያለውን የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ በአዲስ መተካት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (3) መሠረት የሚከተለው ታውጇል:-

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 1156/2011 
ቀን: ነሐሴ 30፥ 2011 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 377/1996

የካቲት 18፥ 1996 ዓ.ም.
የተሻረ