የጤናውን ዘርፍ ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካት ለሚከናወነው በውጤት ላይ የተመሰረተ ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 8 ሚሊዮን ዩሮ (ስምንት ሚሊዮን ዩሮ) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በጣሊያን ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል የካቲት 26 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዚያ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 12550 ኣና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•