በአገልግሎት ላይ

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች የደህንነት ማረጋገጫና ቁጥጥር አዋጅ

ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሀገርን ምርታማነትና ውጤታማነት በማሳደግ እና የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ በማሻሻል ለሀገር ዘላቂ ልማት የሚያበረክተውን አዎንታዊ አስተዋፅፆ ደህንነቱ በተረጋገጠ መልኩ ማስቀጠል ተገቢ በመሆኑ፤

ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች ዕድገትና መራቀቅ ጋር ተያይዘው የሚመጡ አሉታዊ ተፅዕኖች በሀገራዊ የኢንፎርሜሽን ሀብቶች ደህንነት እንዲሁም በዜጎች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ጥቃቶችን አስቀድሞ መከላከልና መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የኢንፎርሜሽን ደህንነት ስጋት የሚፈጥሩ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶችን ወደ ሀገር ውስጥ በሚያስገቡ፣ ከሀገር በሚያስወጡ፣ እንዲሁም በተለያየ መልኩ ጥቅም ላይ በሚያውሉ ተዋንያን ላይ ግልፅ ኃላፊነት መደንገግ በማስፈለጉ፤

ወደሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የሚከለከሉ እና በገደብ የሚገቡ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶችን ለመለየት፣ የደህንነት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓትን ለመወሰን እና በምርቶቹ ላይ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል ግልፅ፣ ወጥ እና ፍትሃዊ አሠራር መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የተከለከሉ እና ገደብ የተጣለባቸው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶችን ከሕግ ውጭ ወይም አግባብነት ያለውን የደህንነት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይዙ ቁጥጥር በሚደረግባቸው ተግባራት በተሰማራ ሰው ላይ ተገቢ የእርምት እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ሕግ መደንገግ አስፈላጊ በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ ፶፭ ንዑስ አንቀፅ (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 1310/2016
ቀን: የካቲት 27፥ 2016 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 548/1999

ነሐሴ 29፥ 1999 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 70/1993

ጥር 28፥ 1993 ዓ.ም.
የተሻረ